Daily Weather Report 26 July 13
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ በሰሜን ምዕራብ፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በምስራቅ፣ በመካከለኛዉ፣ በደቡብ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ምዕራብ ሐረርጌ፣ ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ባሌ፣ አሶሳ፣ መተከል፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ አኝዋክ፣ ማጃንግ፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ማዕከላዊ ትግራይ እና በምስራቅ ጎጃም ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በአይራ36.0፣ በቦሬ 58.8፣ በሊሙ ገነት 62.7 እና በኦቦመርጋ 36.3 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር፣ በመልካ ጀብዱ፣ ድሬዳዋ፣ ኑራኤራ፣ ጨፋ፣ አዋሽ አርባ፣ ቀብሪደሃር፣ ጎዴ እና መተሐራ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.2-43.8°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday there were cloudy conditions across our country in the west, northwest, northeast, east, central, south and southwest. Along with that, light to moderate rainfall was recorded in Jimma, Ilubabor,Buno Bedelle, Horo Guduru, west and east Wollega, Mirab Hararghe, South West Shewa, Arsi and West Arsi, Bale, Assosa, Metekel, West Omo, Sheka, Bench Sheko, Agnuak, Majang, Southern and Central Gondar, Awi Zone, Central Tigray and East Gojjam zones; heavy rainfall amounts were registered at Ayira (36.0 mm), Bore (58.8 mm), Limu Genet (62.7 mm) and Obomerga (36.3 mm). On the other hand, very high daily maximum temperatures ranging from 35.2–43.8°C were recorded in Semera, Elidar, Melka Jebdu, Dire Dawa, Nuraera, Cheffa, Awash Arba, Kebridahar, Gode and Metehara.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በሰሜን፣ ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብ እና በመካከለኛዉ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ባሌ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ዋግኸምራ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፣ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ፣ ማዕከላዊና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች ፤ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኢታንግ፣ ኑዌር እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከቤኒሸንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባሰኬቶ እና ጌዲኦ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በደቡብና ሰሜን ጎንደር፣ ምስራቅ ጎጃም፣ ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብና ማዕከላዊ ትግራይ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምስራቅ ወለጋ እና ምዕራብ ሸዋ ዞኖች ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ በመልካ ጀብዱ፣ ማይሀንሳ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ፣ መተማ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ቀብሪደሃር፣ ጎዴ፣ ጭፍራ እና መተሐራ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡
The kiremt rain producing weather systems will continue to strengthen over the northern, western, northwestern, northeastern, eastern, southwestern, and central parts of the country for tomorrow. In association with this, light to moderate rainfall (1–29 mm) is expected in many areas of Jimma, Illubabor, Buno Bedele, Horo Guduru, Kelem, East and West Wollega, North, East, Southwest and West Shewa, Arsi and West Arsi, Bale, Guji and West Guji zones zones Oromia region; Addis Ababa; West, North, South and Central Gondar, Awi zone, Waghemra, North and South Wollo, West and East Gojjam, the Oromo special zone, and North Shoa of Amhara region; West, Northwest, East, South, Central and Southeast zones of Tigray region; Agnuwak, Itang, Nuwer and Majang zones of Gambela region; Assosa, Metekel, Kamashi and Mao-Komo zones of Benishangul-Gumuz; Gurage, East Gurage, Mareko special zone, Silte, Yem special zone, Halaba, Hadiya, Kembata and Tembaro zones of Central Ethiopia region; Sheka, Bench Sheko, Kaffa, West Omo and Dawuro zones of Southwest Ethiopia region; all zones of Sidama region; and Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo and Gedeo zones of South Ethiopia region. In addition, heavy rainfall exceeding 30 mm within 24 hours is expected over South and North Gondar, East Gojjam, West, Northwest and Central Tigray, Horo Guduru, East Wollega, and West Shoa zones. Meanwhile, daily maximum temperatures ranging between 35 and 40°C will be recorded in Semera, Elidar, Gambela, Fugnido, Abobo, Melka Jebdu, Mayhansa, Mehoni, Dire Dawa, Aysha, Metema, Dallifage, Awash Arba, Kebri Dehar, Gode, Chifra, and Metehara.