Daily Weather Report 26 July 12

Weather Summary for previous day

July 11, 2026

በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ በሰሜን ምዕራብ፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በምስራቅ፣ በመካከለኛዉ፣ በደቡብ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በአዲስ አበባ፤ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምስራቅ ወለጋ፣ ምዕራብ ሐረርጌ፣ ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ባሌ፣ መተከል፣ ሀዋሳ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ቤንች ሸኮ፣ ዳውሮ፣ ወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ሰሜንና ማዕከላዊ ጎንደር እና በምስራቅ ጎጃም ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በፉኝዶ፣ ድሬዳዋ እና መተሐራ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ37.0-39.0°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday cloudy skies were observed over the western, northwest, north‑east, eastern, central, southern and southwest parts of the country. In addition, light to moderate rainfall was recorded in Addis Ababa, Jimma, Illubabor, Horo Guduru, East Wollega, West Hararghe, Southwest Shewa, West Arsi, Bale, Metekel, Hawassa, West Omo, Bench Sheko, Dawuro, Wolaita, Gamo, Gofa, North and Central Gondar, and East Gojjam zones. On the other hand, very high daytime temperatures were recorded in Fogera, Dire Dawa and Metehara, with values between 37.0°C and 39.0°C.

Weather Forecast for next day

July 13, 2026

በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በሰሜን፣ ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብ እና በመካከለኛዉ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ ይበልጥ ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብ ሐረርጌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ባሌ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ዋግኸምራ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፣ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ፣ ማዕከላዊና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች ፤ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኢታንግ፣ ኑዌር እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከቤኒሸንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባሰኬቶ እና ጌዲኦ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በደቡብ ጎንደር፣ ምዕራብ ጎጃም፣ ሰሜንና ምዕራብ ሸዋ ዞኖች ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ በመልካ ጀብዱ፣ ማይሀንሳ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ፣ መተማ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ቀብሪደሃር፣ ጎዴ፣ ጭፍራ እና መተሐራ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡

The kiremt rain bearing weather systems will continue to strengthen over the northern, western, northwestern, northeastern, eastern, southwestern, and central parts of the country for tomorrow. In associating with this, most places of Jimma, Ilubabor, Buno Bedelle, Horo Guduru, Kellem, East and West Wollega, North, East, Southwest and West Shoa, West Hararghe, Arsi and West Arsi, Bale, Guji and West Guji zones of the Oromia region; Addis Ababa; West, North, South and Central Gondar, Awi zone, Waghemra, North and South Wollo, West and East Gojjam, Oromia special zone and North Shewa zones of the Amhara region; West, Northwest, East, South, Central and Southeast zones of Tigray region; Agnuwak, Itang, Nuwer and Majang zones of Gambella region; Assosa, Metekel, Kamashi and Mao-Komo zones of Benishangul-Gumuz region; Gurage, East Gurage, Mareko special zone, Silte, Yem special zone, Halaba, Hadiya, Kembata and Tembaro zones of the Central Ethiopia region; Sheka, Bench Sheko, Kaffa, Konta, West Omo and Dawuro zones of Southwest Ethiopia region; all zones of the Sidama region; and Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo and Gedeo zones of South Ethiopia region will receive light to moderate rainfall (1–29 mm). In addition, heavy rainfall above 30 mm within 24 hours is expected over South Gondar, West Gojam, North and West Shoa zones. On the other hand, daily maximum temperatures are expected to be recorded between 35 and 40 degrees Celsius in Semera, Elidar, Gambella, Fugnido, Abobo, Melka Jebdu, Mayhansa, Mehoni, Dire Dawa, Aysha, Metema, Dallifage, Awash Arba, Kebri Dehar, Gode, Chifra, and Metehara.