Daily Weather Report 26 July 11

Weather Summary for previous day

July 10, 2026

በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ በሰሜን ምዕራብ፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በምስራቅ፣ በመካከለኛዉ፣ በደቡብ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በአዲስ አበባ፤ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምስራቅ፣ ምዕራብ አርሲ፣ አሶሳ፣ መተከል፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ዳውሮ፣ ወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ አኝዋክ፣ ማጃንግ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ዋግኸምራ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜን ሸዋ እና በምስራቅ ትግራይ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በጋምቤላ 65.6፣ በአማን 51.9 እና በሀዋሳ 35.6ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በመተማ፣ መንደር11፣ ጋምቤላ፣ ድሬዳዋ እና መተሐራ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ36.0-36.6°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday clouds were observed over our country’s western, northwestern, northeastern, eastern, central, southern and southwestern areas. Correspondingly, Addis Ababa; Jimma; Illubabor; Buno Bedele; Kellem; East and West Wollega; North, East and West Arsi; Assosa; Metekel; Sheka; Bench Sheko; Kefa; Dawuro; Wolaita; Gamo; Gofa; Agnuak; Majang; West, North, South and Central Gondar; Awi zone; Wag Hemra; North and South Wollo; East Gojjam; North Shewa; and the eastern zones of Tigray received light-to-moderate rainfall. Heavy rainfall was recorded in Gambela (65.6 mm), Aman (51.9 mm) and Hawassa (35.6 mm). Meanwhile, high daytime temperatures between 36.0–36.6°C were recorded in Metehara, Mender11, Gambela, Dire Dawa and Metehara.

Weather Forecast for next day

July 12, 2026

በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በሰሜን፣ ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብ እና በመካከለኛዉ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብ ሐረርጌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ባሌ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ዋግኸምራ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፣ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ፣ ማዕከላዊና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች ፤ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኢታንግ፣ ኑዌር እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከቤኒሸንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባሰኬቶ እና ጌዲኦ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በሆሮ ጉዱሩ፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ ማዕከላዊ ትግራይ፣ ሰሜንና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ አሶሳ፣ መተከል እና ካማሽ ዞኖች ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ በመልካ ጀብዱ፣ ማይሀንሳ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ፣ መተማ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ቀብሪደሃር፣ ጎዴ፣ ጭፍራ እና መተሐራ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡

Weather conditions favorable for kiremt rainfall will continue to strengthen over the northern, western, northwestern, northeastern, eastern, southwestern, and central parts of the country for tomorrow. As a result, most places of Jimma, Ilubabor, Buno Bedelle, Horo Guduru, Kellem, East and West Wollega, North, East, Southwest and West Shoa, West Hararghe, Arsi and West Arsi, Bale, Guji and West Guji zones of Oromia region, Addis Ababa; West, North, South and Central Gondar, Awi zone, Waghemra, North and South Wollo, West and East Gojjam, and North Shewa zones of Amhara region; West, Northwest, East, South, Central and Southeast zones of Tigray region; Agnuwak, Itang, Nuwer and Majang zones of Gambella region; Assosa, Metekel, Kamashi and Mao-Komo zones of Benishangul-Gumuz region; Gurage, East Gurage, Mareko special zone, Silte, Yem special zone, Halaba, Hadiya, Kembata and Tembaro zones of Central Ethiopia region; Sheka, Bench Sheko, Kaffa, Konta, West Omo and Dawuro zones of Southwest Ethiopia region; all zones of the Sidama region; and Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo and Gedeo zones of South Ethiopia region will experience light to moderate rainfall (1–29 mm). In addition, heavy rainfall exceeding 30 mm within 24 hours is expected over Horo Guduru, East and West Wollega, Southwest and West Shoa, Central Tigray, North and Central Gondar, West Gojjam, Awi zone, Assosa, Metekel and Kamashi zones. On the other hand, daily maximum temperatures are expected to be recorded between 35 and 40 degrees Celsius in Semera, Elidar, Gambella, Fugnido, Abobo, Melka Jebdu, Mai Hansa, Mehoni, Dire Dawa, Aysha, Metema, Dallifage, Awash Arba, Kebri Dehar, Gode, Chifra, and Metehara.