Daily Weather Report 26 July 10
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ በሰሜን ምዕራብ፣ በሰሜን ምስራቅ፣ ምስራቅ፣ በመካከለኛዉ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በአዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ሐረሪ፤ ኢሉባቦር፣ ምስራቅ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ባሌ፣ ቦረና፣ አሶሳ፣ መተከል፣ ከፋ፣ ወላይታ፣ ጋሞ፣ አውሲ፣ ሲቲ፣ ፋፈን፣ አኝዋክ፣ ማጃንግ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ዋግኸምራ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜን ሸዋ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ምስራቅና ማዕከላዊ ትግራይ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በአይከል 32.0፣ በቢሾፍቱ 32.0፣ በአዳማ 30.9፣ በባቱ 35.5፣ በዴኔባ 50.2፣ በአዲስ ዘመን 39.9፣ በመካነ ኢየሱስ 44.6 እና በወርቅ አምባ 34.7 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በመልካ ጀብዱ፣ ድሬዳዋ፣ መሆኒ፣ ሰመራ፣ ኤሊዳር፣ አዋሽ አርባ፣ አይሻ፣ መንደር11፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ እና መተሐራ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.4-44.8°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday there were clouds over the western, northwestern, northeastern, eastern, central and southwestern parts of the country. In addition, Addis Ababa, Dire Dawa, Harari, Ilubabor, East Wollega, North Wollega, East Wollega, South West Shewa and West Shewa, West and East Hararghe, Arsi and West Arsi, Bale, Borena, Assosa, Metekel, Kefa, Wolaita, Gamo, Awsi, Sitti, Fafen, Agnuak, Majang, western, northern, southern and central Gondar, Awi zone, Wag Hemra, North and South Wollo, West and East Gojjam, North Shewa, North West, East and Central Tigray zones received light to moderate rainfall. Heavy rainfall amounts were recorded in Aykel 32.0 mm, Bishoftu 32.0 mm, Adama 30.9 mm, Batu 35.5 mm, Deneba 50.2 mm, Addis Zemen 39.9 mm, Makenna Iyesus 44.6 mm and Workamba 34.7 mm. Meanwhile, in Melka Jebdu, Dire Dawa, Mehoni, Semera, Elidar, Awash Arba, Aisha, Mender 11, Gambella, Funyido and Metehara the daytime maximum temperatures ranged from 35.4°C to 44.8°C.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በሰሜን፣ ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብ እና በመካከለኛዉ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ባሌ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ሐረሪ፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ዋግኸምራ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፣ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ፣ ማዕከላዊና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች ፤ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኢታንግ፣ ኑዌር እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከቤኒሸንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የአውሲ፣ ጋቢ እና ሀሪ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የሲቲ እና ፋፈን ዞኖች፣ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባሰኬቶ እና ጌዲኦ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በጅማ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምስራቅ ወለጋ፣ ቡኖ በደሌ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ ሰሜን ምዕራብና ማዕከላዊ ትግራይ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ካማሽ እና ጉራጌ ዞኖች ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ በመልካ ጀብዱ፣ ማይሀንሳ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ፣ መተማ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ቀብሪደሃር፣ ጎዴ፣ ጭፍራ እና መተሐራ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡
The following day, weather conditions favorable for winter rain will persist over northern, western, northwestern, northeastern, eastern, southwestern and central parts of the country. In connection with this, heavy precipitation (1–29 mm) is expected in many areas of the following zones: from Oromia Region Jimma, Illubabor, Buno Bedele, Horo Guduru, Kellem, East and West Wollega, North, East, Southwest and West Shewa, East and West Hararghe, Arsi and West Arsi, Bale, Guji and West Guji; Addis Ababa; Dire Dawa; Harari; from Amhara Region West, North, South and Central Gondar, Awi zone, Wag Hemra, North and South Wollo, West and East Gojjam, the Oromia Special Zone and North Shewa zones; from Tigray Region West, Northwest, Northeast, South, Central and Southeast zones; from Gambela Region Agnuak, Itang, Nuer and Majang zones; from Benishangul-Gumuz Asosa, Metekel, Kamashi and Mao-Komo zones; from Afar Region Awsi, Gabi and Hari zones; from Somali Region Siti and Fafan zones; from Central Ethiopia Region Gurage, East Gurage, the Mareko special zone, Silte, the special zone of M, Halaba, Hadiya, Kembata and Tembaro zones; from South West Ethiopia region Sheka, Bench Sheko, Kaffa, Konta, West Omo and Dawuro zones; all zones of Sidama Region; from Southern Ethiopia region Wolayita, Gamo, Gofa, Basketo and Gedeo zones. Rainfall amounts will range from light to moderate (1–29 mm) in many of these places. Additionally, heavy rain exceeding 30 mm within 24 hours is expected over Jimma, Horo Guduru, East Wollega, Buno Bedele, Southwest and West Shewa, North Wollo and Central Tigray, West, North, South and Central Gondar, West Gojjam, Awi zone, Kamashi and Gurage zones. Elsewhere, daytime maximum temperatures of 35–40°C are expected and will be recorded in Semera, Elidar, Gambela, Fugnido, Abobo, Melka Jebdu, Mayhansa, Mehoni, Dire Dawa, Aisha, Metema, Dallifage, Awash Arba, Kebridahar, Gode, Chifra and Metehara.