Daily Weather Report 26 July 09
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ በሰሜን ምዕራብ፣ በሰሜን ምስራቅ፣ ምስራቅ፣ በመካከለኛዉ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በአዲስ አበባ፤ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ምስራቅና ምዕራብ ሸዋ፣ መተከል፣ ቤንች ሸኮ፣ ወላይታ፣ ሀዋሳ፣ ሲቲ፣ ማጃንግ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ዋግኸምራ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜን ሸዋ፣ ሰሜን ምዕራብና ደቡብ ትግራይ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በቢሾፍቱ 33.1 እና አትናጎ 46.2 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በመልካ ጀብዱ፣ ድሬዳዋ፣ ማይሀንሳ፣ ሰመራ፣ ኤሊዳር፣ አዋሽ አርባ፣ አይሻ፣ ባቲ፣ መተማ፣ ጎዴ፣ መተሐራ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.0-45.8°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
On the previous day, there were patches of clouds over parts of our country in the west, northwest, north‑east, east, central, and southwest. In addition, Addis Ababa; Jimma; Ilubabor; Buno Bedelle; eastern and western Wollega; eastern and western Shewa; Metekel; Bench Sheko; Wolaita; Hawassa; Sitti; Majang; West, North, South and Central Gondar; Awi zone; Wag Hemra; North and South Wollo; western and eastern Gojjam; North Shewa; northwest and south Tigray zones received light to moderate rainfall, while heavy rainfall was recorded in Bishoftu (33.1 mm) and Atnago (46.2 mm). Elsewhere, in Melka Jebdu, Dire Dawa, Mayhanssa, Semera, Elidar, Awash Arba, Ayesha, Bati, Metema, Gode, Metehara and Kebridahar, daytime maximum temperatures were recorded between 35.0°C and 45.8°C.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በሰሜን፣ ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብ እና በመካከለኛዉ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ ይበልጥ ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ባሌ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ሐረሪ፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ዋግኸምራ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፣ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ፣ ማዕከላዊና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች ፤ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኢታንግ፣ ኑዌር እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከቤኒሸንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የአውሲ፣ ቅልበቲ፣ ጋቢ፣ ሀሪ እና ፋንቲ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የሲቲ እና ፋፈን ዞኖች፣ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባሰኬቶ እና ጌዲኦ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በጅማ፣ ምስራቅ ወለጋ፣ ቡኖ በደሌ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ካማሽ፣ ጉራጌ እና ምዕራብ ሸዋ ዞኖች ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ በመልካ ጀብዱ፣ ማይሀንሳ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ፣ መተማ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ቀብሪደሃር፣ ጎዴ፣ ጭፍራ እና መተሐራ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡
The Kiremt rain-bearing weather systems are expected to be strengthen further over the northern, western, northwestern, northeastern, eastern, southwestern, and central regions of the country in the coming days. As a result, light to moderate rainfall (ranging from 1 to 29 mm) is expected across various areas, including Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Horo Guduru, Kelem, East and West Wollega, North, East, Southwest, and West Shoa, West and East Hararghe, Arsi and West Arsi, Bale, Guji, and West Guji zones in the Oromia region; as well as Addis Ababa, Dire Dawa, and Harari; the West, North, South, and Central Gondar, Awi zone, Wag Hemra, North and South Wollo, West and East Gojjam, the Oromo special zone, and North Shoa in the Amhara region; the West, Northwest, East, South, Central, and Southeast zones of Tigray; Agnuak, Itang, Nuwer, and Majang zones in Gambella; Assosa, Metekel, Kamashi, and Mao-Komo zones in Benishangul-Gumuz; Awsi, Kilbeti, Gabi, Hari, and Fanti zones in Afar; Siti and Fafan zones in Somali; and Gurage, East Gurage, Mareko Special Zone, Silte, Yem Special Zone, Halaba, Hadiya, Kembata, and Tembaro zones in Central Ethiopia; Sheka, Bench Sheko, Kaffa, Konta, West Omo, and Dawuro zones in Southwest Ethiopia; all zones of Sidama; and Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, and Gedeo zones in South Ethiopia. Additionally, we should prepare for heavy rainfall exceeding 30 mm within 24 hours in areas like Jimma, East Wollega, Buno Bedele, West, North, South, and Central Gondar, West Gojjam, Awi zone, Kamashi, Gurage, and West Shoa zones. On the flip side, daytime maximum temperatures are expected to soar between 35 to 40°C in places like Semera, Elidar, Gambella, Fugnido, Abobo, Melka Jebdu, Mayhansa, Mehoni, Dire Dawa, Ayisha, Metema, Dallifage, Awash Arba, Kebri Dehar, Gode, Chifra and Metehara.