Daily Weather Report 26 July 08

Weather Summary for previous day

July 7, 2026

በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ በሰሜን ምዕራብ፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛዉ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በአዲስ አበባ፤ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ አሶሳ፣ መተከል፣ ማጃንግ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ዋግኸምራ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜን ሸዋ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብና ማዕከላዊ ትግራይ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በቻግኒ 49.2፣ ቡሌን 45.4፣ሻምቡ 34.2፣ በዴሌ 52.0፣ ሺንዲ 46.5 እና በአዲስ ዘመን 38.6 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በፉኝዶ፣ በመልካ ጀብዱ፣ ድሬዳዋ፣ ማይሀንሳ፣ ሰመራ፣ ኤሊዳር፣ አዋሽ አርባ፣ ጭፍራ፣ ጨፋ፣ ጎዴ፣ መተሐራ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.0-44.8°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, cloudy skies prevailed over our country’s western, northwestern, northeastern, central and southwestern areas. In addition, heavy rainfall was recorded in Addis Ababa; Jimma; Ilubabor; Buno Bedele; Kelem; East and West Wollega; North, South, West and Central Wollo; Assosa; Metekel; Majang; West, North, South and Central Gondar; Awi Zone; Wag Hemra; North and South Wollo; West and East Gojjam; North Shewa; Northwest, South and Central zones of Tigray, with amounts ranging from light to moderate. Local totals included 49.2 mm at Chagni, 45.4 mm at Bullen, 34.2 mm at Shambu, 52.0 mm at Bedelle, 46.5 mm at Shindi and 38.6 mm at Addis Zemen. Elsewhere, high daytime temperatures were recorded at Fugnido, Melka Jebdu, Dire Dawa, May Hansa, Semera, Elidar, Awash Arba, Chifra, Chefa, Gode, Metehara and Kebridahar, ranging from 35.0°C to 44.8°C.

Weather Forecast for next day

July 9, 2026

በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በሰሜን፣ ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብ እና በመካከለኛዉ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ባሌ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ሐረሪ፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ዋግኸምራ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፣ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ፣ ማዕከላዊና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኢታንግ፣ ኑዌር እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከቤኒሸንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የአውሲ፣ ቅልበቲ፣ ጋቢ፣ ሀሪ እና ፋንቲ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የሲቲ እና ፋፈን ዞኖች፣ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባሰኬቶ እና ጌዲኦ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በጅማ፣ ደቡብ ጎንደር፣ የም ልዩ ዞን፣ ጉራጌ እና አርሲ ዞኖች ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ በመልካ ጀብዱ፣ ማይሀንሳ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ፣ መተማ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ቀብሪደሃር፣ ጎዴ፣ ጭፍራ እና መተሐራ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡

Tomorrow, the weather systems favorable for the formation of the Kiremt rainfall will continue to strengthen over the northern, western, northwestern, northeastern, eastern, southwestern, and central parts of the country. Accordingly, light to moderate rainfall (1–29 mm) is expected over many areas of Jimma, Illubabor, Buno Bedele, Horo Guduru, Kellem, East and West Wollega, North Shoa, East Shoa, Southwest Shoa, West Shoa, East and West Hararghe, Arsi, West Arsi, Bale, Guji, and West Guji zones of the Oromia region; Addis Ababa; Dire Dawa; the Harari region; West Gondar, North Gondar, South Gondar, Central Gondar, Awi zone, Wag Hemra, North Wollo, South Wollo, West Gojjam, East Gojjam, the Oromo special zone, and North Shoa zones of the Amhara region; West, Northwest, East, South, Central, and Southeast Zones of the Tigray region; Agnuwak, Itang, Nuer, and Majang zones of the Gambella region; Assosa, Metekel, Kamashi, and Mao-Komo Zones of the Benishangul-Gumuz region; Awsi, Kilbati, Gabi, Hari, and Fanti zones of the Afar region; Sitti and Fafan zones of the Somali region; Gurage, East Gurage, Mareqo Special Zone, Silte, Yem special zone, Halaba, Hadiya, Kembata, and Tembaro zones of the Central Ethiopia region; Sheka, Bench Sheko, Kaffa, Konta, West Omo, and Dawuro Zones of the Southwest Ethiopia Region; all zones of the Sidama region; and Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, and Gedeo zones of the South Ethiopia region. In addition, heavy rainfall exceeding 30 mm within 24 hours is expected over Jimma, South Gondar,Yem special zone, Gurage, and Arsi zones. On the other hand, maximum daytime temperatures ranging from 35°C to 40°C are expected to be recorded in Semera, Elidar, Gambella, Fugnido, Abobo, Melka Jebdu, May Hansa, Mehoni, Dire Dawa, Aisha, Metema, Dallifage, Awash Arba, Kebri Dehar, Gode, Chifra, and Metehara.