Daily Weather Report 26 July 07

Weather Summary for previous day

July 6, 2026

በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ በሰሜን ምዕራብ፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛዉ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በአዲስ አበባ፤ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ማጃንግ፣ አኝዋክ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ዋግኸምራ፣ ሰሜን፣ ደቡብ፣ ምዕራብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ምስራቅና ማዕከላዊ ትግራይ፣ ዳውሮ እና ቤንች ሸኮ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በነቀምቴ 38.6 እና በቡሬ 45.0ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በፉኝዶ፣ በመልካ ጀብዱ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ፣ ዴጋን፣ ማይሀንሳ፣ መሆኒ፣ መተማ፣ ጎዴ፣ መተሐራ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.0-41.5°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday there were widespread cloudy patches over western, northwestern, northeastern, central and southwestern parts of the country. In addition, Addis Ababa, Jimma, Illubabor, Buno Bedelle, Kellem, East and West Wollega, Majang, Agnuak, West and East Gojjam, Awi zone, Wag Hemra, North, South, West and Central Gondar, Northwestern, Eastern and Central Tigray, Dawuro and Bench Sheko zones received light to moderate rainfall; heavy amounts were recorded at Nekemte with 38.6 mm and at Bure with 45.0 mm. On the other hand, high daytime temperatures ranging from 35.0–41.5°C were recorded in Funyido, Melka Jebdu, Dire Dawa, Aysha, Degan, Mayhansa, Mehoni, Metema, Gode, Metehara and Kebridahar.

Weather Forecast for next day

July 8, 2026

በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በሰሜን፣ ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብ እና በመካከለኛዉ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ ይበልጥ ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ባሌ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ዋግኸምራ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፣ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ፣ ማዕከላዊና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኢታንግ፣ ኑዌር እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከቤኒሸንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የአውሲ፣ ቅልበቲ፣ ጋቢ፣ ሀሪ እና ፋንቲ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የሲቲ ዞን፣ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ዳውሮ፣ ሸካ እና ቤንች ሸኮ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጎፋ፣ ወላይታ እና ጌዴኦ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በጅማ፣ ምስራቅ ጎጃም፣ ደቡብ ጎንደር፣ ሰሜን እና ምዕራብ ሸዋ ዞኖች ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ በመልካ ጀብዱ፣ ማይሀንሳ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ፣ መተማ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ቀብሪደሃር፣ ጭፍራ እና መተሐራ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡

Tomorrow, weather conditions favorable for winter rains will persist mainly over northern, western, northwestern, northeastern, eastern, and southwestern and central parts of the country. In addition, rainfall (light to moderate, 1–29 mm) is expected in many areas of the Oromia region including Jimma, Ilubabor, Buno Bedelle, Horo Guduru, Kellem, East and West Wollega, North, East, Southwest and West Shewa, East and West Hararghe, Arsi and West Arsi, Bale, Guji and West Guji zones; Addis Ababa; Dire Dawa; from Amhara region in the West, North, South and Central Gondar zones, Awi zone, Waghemra, North and South Wollo, West and East Gojjam, the Oromia Special Zone and North Shewa zones; from Tigray region in the West, Northwest, East, South, Central and Southeastern zones; from Gambela region in Agnuak, Itang, Nuer and Majang zones; from Benishangul-Gumuz in Asosa, Metekel, Kamashi and Mao-Komo zones; from Afar region in Awsi, Kilbet, Gabi, Hari and Fanti zones; from Somali region in the Sitti zone; from Central Ethiopia region in Gurage, East Gurage, Mareko special zone, Silte, Yem special zone, Hadiya, Kambata and Tambaro zones; from Southwest Ethiopia region in Kefa, Dawuro, Sheka and Bench Sheko zones; the zones of Sidama region; and from Southern Ethiopia region in Gofa, Wolayita and Gedeo zones. In many of these places rainfall amounts will range from light to moderate (1–29 mm). Furthermore, heavy rainfall exceeding 30 mm within 24 hours is expected over Jimma, East Gojjam, South Gondar, and the North and West Shewa zones. On the other hand, daytime maximum temperatures between 35 and 40 degrees Celsius will be recorded in Semera, Elidar, Gambela, Fugnido, Abobo, Melka Jebdu, Mayhanssa, Mehoni, Dire Dawa, Aisha, Metema, Dallifage, Awash Arba, Kebridahar, Chifra and Metehara.