Daily Weather Report 26 July 06
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ በሰሜን ምዕራብ፣ በመካከለኛዉ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ አኝዋክ፣ ምስራቅ ጎጃም፣ ደቡብ፣ ምዕራብና ማዕከላዊ እና ቤንች ሸኮ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ፉኝዶ፣ በመልካ ጀብዱ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ፣ ዴጋን፣ ሚኤሶ፣ መተማ፣ ዳሊፋጌ፣ ማይሀንሳ፣ ባቲ፣ መተሐራ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.0-45.0°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday there were haze and cloud cover over the western, northwestern, central and southwestern parts of our country. In addition, light to moderate rainfall was recorded in Jimma, Ilubabor, Buno Bedelle, Kellem, West and East Wollega, East, South West and West Shewa, Agnuak, East Gojam, South, West and Central Gojam and Bench Sheko zones. On the other hand, high daytime temperatures ranging from 35.0–45.0°C were recorded in Semera, Elidar, Fugnido, Melka Jebdu, Dire Dawa, Aisha, Dega, Meiso, Metema, Dallifage, Mayhansa, Bati, Metehara and Kebridahar.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በሰሜን፣ ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብ እና በመካከለኛዉ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብ ሐረርጌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ባሌ፣ ምስራቅ ቦረና፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ዋግኸምራ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፣ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ፣ ማዕከላዊና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኢታንግ፣ ኑዌር እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከቤኒሸንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የአውሲ እና ፋንቲ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ እና ቤንች ሸኮ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ እና ጌዴኦ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በሆሮ ጉዱሩ፣ ምስራቅ ወለጋ፣ ሰሜን ምዕራብና ማዕከላዊ ትግራይ፣ ሰሜን፣ ምዕራብና ደቡብ ጎንደር እና ምዕራብ ሸዋ ዞኖች ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ በመልካ ጀብዱ፣ ማይሀንሳ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ፣ መተማ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ጎዴ፣ ቀብሪደሃር፣ ጭፍራ እና መተሐራ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡
The weather conditions favorable for Kiremt rainfall will continue to intensify over the northern, western, northwestern, northeastern, eastern, southwestern, and central parts of our country for tomorrow. In association with this, light to moderate rainfall (1–29 mm) is expected over most areas of Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Horo Guduru, Kelem, East and West Wollega, North, East, Southwest and West Shoa, West Hararghe, Arsi and West Arsi, Bale, East Borena, Guji and West Guji zones of Oromia region; Addis Ababa; West, North, South and Central Gondar, Awi zone, Wag-Hemra, North and South Wollo, West and East Gojjam, the Oromo special zone, and North Shoa zones of Amhara region; West, Northwest, East, South, Central and Southeast zones of Tigray region; Agnuak, Itang, Nuwer and Majang zones of Gambella region; Assosa, Metekel, Kamashi and Mao-Komo zones of Benishangul-Gumuz; Awsi and Fanti zones of Afar region; Gurage, East Gurage, Mareko special zone, Silte, Yem special zone, Hadiya, Kembata and Tembaro zones of Central Ethiopia region; Kaffa, Sheka and Bench Sheko zones of Southwest Ethiopia region; the zones of Sidama region; and Wolaita and Gedeo zones of South Ethiopia Region. In addition, Horo Guduru, East Wollega, Northwest and Central Tigray, North, West and South Gondar, and West Shoa zones will receive heavy rainfall exceeding 30 mm within 24 hours. On the other hand, daily maximum temperatures of 35–40°C will be recorded in Semera, Elidar, Gambella, Fugnido, Abobo, Melka Jebdu, Mai Hansa, Mehoni, Dire Dawa, Aysha, Metema, Dallifage, Awash Arba, Godey, Kebri Dehar, Chifra, and Metehara.