Daily Weather Report 26 July 05

Weather Summary for previous day

July 4, 2026

በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ በሰሜን ምዕራብ፣ በመካከለኛዉ እና በደቡብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ሰሜን ጎንደር፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምስራቅ ወለጋ፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ሸዋ እና ቡርጂ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል:: በሌላ በኩል በባቲ፣ ጨፋ፣ ድሬዳዋ እና መተሐራ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.0-40.0°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, the western, northwestern, central, and southern areas of our country had cloud cover. In connection with this, North Gondar, Jimma, Illubabor, Horo Guduru, East Wollega, West and East Shewa, and Burji zones received a light to moderate amount of rainfall. On the other hand, the daily maximum temperature was recorded between 35.0°C and 40.0°C in Bati, Chefa, Dire Dawa, and Metehara.

Weather Forecast for next day

July 6, 2026

በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር አመቺ ሁኔታን የሚፈጥሩ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በምዕራብ፣ ሰሜን፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ፣ ደቡብ ምዕራብ እና በመካከለኛዉ ላይ ይበልጥ እንደሚጠናከሩ የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ማዕከላዊ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ማዕከላዊና ደቡብ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ዋግኽምራ፣ የኦሮሞ ብሔረሰብ ልዩ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምስራቅ፣ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ባሌ፣ አዲስ አበባ፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ፣ ማጃንግ እና ኢታንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ምስራቅ ጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ኮንታ እና ጌዲኦ እና የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከአፋር ክልል የአውሲ እና ፋንቲ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ሰሜን ምዕራብ፣ማዕከላዊ፣ ምስራቅ ትግራይ፣ ሰሜን፣ ደቡብ ጎንደር፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ጎጃም፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ እና ምዕራብ አርሲ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ በመልካ ጀብዱ፣ ማይሀንሳ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ፣ መተማ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ቀብሪደሃር፣ ጭፍራ እና መተሐራ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡

The rain producing meteorological systems favorable for Kiremt rainfall development will further strengthen over the western, northern, northwestern, northeastern, eastern, southern, southwestern, and central parts of the country. In connection with this, most places in the West, Northwest, Central, East, South, and Southeast zones of the Tigray Region; West, North, Central, and South Gondar, Awi zone, West and East Gojjam, North and South Wollo, Waghemra, Oromo Nationality special zone, and North Shewa zones of the Amhara Region; Asosa, Kamashi, and Mao-Komo zones of the Benishangul-Gumuz Region; Jimma, Illubabor, Buno Bedele, Kelem, Horo Guduru, West and East Wollega, North, East, West, and Southwest Shewa, Arsi and West Arsi, West and East Hararghe, and Bale zones of the Oromia Region and Addis Ababa; Anywaak, Majang, and Itang zones of the Gambella Region; Bench Sheko, Sheka, Keffa, West Omo, and Dawro zones of the Southwest Ethiopia Region; Gurage, East Gurage, Silte, Hadiya, Halaba, Yem special zone, Kembata, and Tembaro zones of the Central Ethiopia Region; Wolaita, Gofa, Gamo, Konta, and Gedeo zones of the South Ethiopia Region; zones of the Sidama Region; and Awsi and Fanti zones of the Afar Region will receive light to moderate rainfall 1- 29 mm. Additionally, Northwest, Central, and East Tigray; North and South Gondar; West and East Gojjam; Horo Guduru; West and Southwest Shewa; and West Arsi zones will receive heavy rainfall of over 30 mm within 24 hours. On the other hand, the maximum daily temperature is expected to be recorded between 35°C and 40°C in Semera, Elidar, Gambella, Fugnido, Abobo, Melka Jebdu, Mayhanssa, Mehoni, Dire Dawa, Aisha, Metema, Dallifage, Awash Arba, Kebridahar, Chifra, and Metehara.