Daily Weather Report 26 July 04
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ በሰሜን ምዕራብ፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛዉ እና በደቡብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ምስራቅ ትግራይ፣ በምዕራብ፣ ሰሜን፣ ማዕከላዊና ደቡብ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ምዕራብ ሸዋ፣ምዕራብ ጎጃም፣ወላይታ፣ ጎፋ፣ ጌዲኦ እና ቡርጂ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በነቀምቴ 61.0 እና ጎንደር 40.1 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል ድሬዳዋ፣ ሚኤሶ፣ መተሐራ እና መተማ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ36.6-38.4°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, the western, northwestern, northeastern, central, and southern areas of our country had cloud cover. In connection with this, East Tigray, West, North, Central, and South Gondar, Awi zone, Jimma, Illubabor, Horo Guduru, East and West Wollega, West Shewa, West Gojjam, Wolaita, Gofa, Gedeo, and Burji zones received a light to moderate (1-29 mm), while a heavy amount of rainfall of 61.0 mm in Nekemte and 40.1 mm in Gondar was recorded. On the other hand, the daily maximum temperature was recorded from 36.6 to 38.4°C in Dire Dawa, Meiso, Metehara, and Metema.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በምዕራብ፣ ሰሜን፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ፣ ደቡብ ምዕራብ እና በመካከለኛዉ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ ጠንካራና የተስፋፋ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ማዕከላዊ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ ፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ማዕከላዊና ደቡብ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ዋግኽምራ፣ የኦሮሞ ብሔረሰብ ልዩ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የ መተከል፣ አሶሳ፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምስራቅ፣ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብ ሐረርጌ፣ምዕራብ ጉጂ ፣ባሌ፣ አዲስ አበባ፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ፣ ማጃንግ እና ኢታንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ምስራቅ ጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ እና ጌዲኦ እና የሲዳማ ክልል ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ሆሮ ጉዱሩ፣ ምስራቅ ወለጋ፣ምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብ ጎጃም እና ምዕራብ አርሲ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ በመልካ ጀብዱ፣ ማይሀንሳ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ፣ መተማ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ቀብሪደሃር፣ ጭፍራ እና መተሐራ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡
Tomorrow, the western, northern, northwestern, northeastern, eastern, southern, southwestern, and central areas of our country will have strong and widespread cloud cover. In connection with this, most places in the West, Northwest, Central, East, South, and South zones of the Tigray Region; West, North, Central, and South Gondar, Awi zone, West and East Gojjam, North and South Wollo, Wag Hemra, Oromo Nationality special zone, and North Shewa zones of the Amhara Region; Metekel, Asosa, Kamashi, and Mao-Komo zones of the Benishangul-Gumuz Region; Jimma, Illubabor, Buno Bedele, Kelem, Horo Guduru, West and East Wollega, North, East, West, and Southwest Shewa, Arsi and West Arsi, West Hararghe, West Guji, Bale zones of the Oromia Region and Addis Ababa; Agnuak, Majang, and Itang zones of the Gambella Region; Bench Sheko, Sheka, Keffa, West Omo, and Dawro zones of the Southwest Ethiopia Peoples' Region; Gurage, East Gurage, Silte, Hadiya, Halaba, Yem special zone, Kembata, and Tembaro zones of the Central Ethiopia Region; Wolaita, Gofa, Gamo, and Gedeo zones of the South Ethiopia Region; and all zones of the Sidama Region will receive light to moderate rainfall ranging from 1 to 29 mm. Additionally, Horo Guduru, East Wollega, West Shewa, West Gojjam, and West Arsi zones will receive heavy rainfall of over 30 mm within 24 hours. On the other hand, the maximum daily temperature is expected to be recorded between 35°C and 40°C in Semera, Elidar, Gambella, Fugnido, Abobo, Melka Jebdu, Mayhanssa, Mehoni, Dire Dawa, Aisha, Metema, Dalifage, Awash Arba, Kebridahar, Chifra, and Metehara.