Daily Weather Report 26 July 02
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ በሰሜን ምዕራብ፣ በሰሜን፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛዉ እና በደቡብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በጅማ፣ ምስራቅ ወለጋ፣ ጉጂ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ማዕከላዊና ሰሜን ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ዳውሮ፣ ጎፋ፣ ወላይታ፣ ስልጤ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ማዕከላዊና ደቡብ ምስራቅ ትግራይ እና ጉራጌ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በነቀምቴ 38.0ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በድሬዳዋ፣ አይሻ፣ ጨፋ፣ መተሐራ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ37.0-40.0°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday there were cloudy conditions in the western, northwestern, northern, northeastern, central, and southern parts of our country. In connection with this, Jima, East Wollega, Guji, West Arsi, West and East Gojjam, Central and North Gondar, Awi Zone, Dawuro, Gofa, Wolayita, Silte, Northwest, Central and Southeast Tigray, and Gurage zones received light to moderate rainfall; Nekemte recorded heavy rainfall measuring 38.0 mm. On the other hand, high daytime temperatures of 37.0–40.0°C were recorded in Dire Dawa, Ayesha, Cheffa, Metehara, and Kebridahar.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በምዕራብ፣ ሰሜን፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ፣ ደቡብ ምዕራብ እና በመካከለኛዉ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ ምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ባሌ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሀረር፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ እና ጌዴኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኢታንግ፣ ኑዌር እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከቤኒሸንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ዋግኸምራ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፣ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ፣ ማዕከላዊና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በኢሉባቦር፣ ምስራቅ ወለጋ፣ ማዕከላዊ ትግራይ፣ ደቡብ ጎንደር፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ ዞኖች ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ በመልካ ጀብዱ፣ ማይሀንሳ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ፣ መተማ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ቀብሪደሃር፣ ጭፍራ እና መተሐራ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡
Tomorrow, weather conditions favorable for winter rain will persist over western, northern, northwestern, north-eastern, eastern, southern, southwestern and central parts of the country. In connection with this, light to moderate rain (1–29 mm) will occur in many areas of the zones of Jimma, Ilubabor, Buno Bedelle, Horo Guduru, Kellem, East and West Wollega, North, East, Southwest and West Shewa, East and West Hararghe, Arsi and West Arsi, Bale, Guji and West Guji in Oromia Region; Addis Ababa; Harari; Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo and Gedeo zones of Southern Ethiopia region; Sidama zones; Gurage, East Gurage, Mareqo special zone, Silte, Yem special zone, Hadiya, Halaba, Kembata and Tambaro zones of the central Ethiopia region zone; Keffa, Sheka, Bench Sheko, Konta, West Omo and Dawuro zones of South West Ethiopia Region; Agnuak, Itang, Nuer and Majang zones of Gambela Region; Asosa, Metekel, Kamashi and Mao Komo zones of Benishangul-Gumuz Region; West, North, South and Central Gondar, Awi zone, Wag Hemra, North and South Wollo, West and East Gojjam, the Oromia Special Zone, and North Shewa zones of Amhara Region; and the western, northwestern, northeastern, eastern, central and southeastern zones of Tigray. Additionally, heavy rain exceeding 30 mm within 24 hours is expected in Ilubabor, East Wollega, Central Tigray, South Gondar, Southwest and West Shewa zones. On the other hand, daytime maximum temperatures between 35 and 40 degrees Celsius will be recorded in Semera, Elidar, Gambela, Funyido, Abobo, Melka Jebdu, Mayhanssa, Mehoni, Dire Dawa, Aisha, Metema, Dallifage, Awash Arba, Kebridahar, Chifra and Metehara.