Daily Weather Report 26 July 01
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ በሰሜን ምዕራብ፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛዉ እና በደቡብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በአዲስ አበባ፤ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ምስራቅ ወለጋ፣ ጉጂ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜን ጎንደር፣ ወላይታ፣ ማጃንግ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብና ደቡብ ምስራቅ ትግራይ እና ጉራጌ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በቦሬ 41.5 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በመልካ ጀብዱ፣ ማይሀንሳ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ፣ ጭፍራ፣ ጨፋ፣ ባቲ፣ መተማ፣ ሰመራ፣ ኤሊዳር፣ አዋሽ አርባ፣ መተሐራ፣ ዳሊፋጌ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.0-44.0°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday there were cloud patches over the western, northwestern, northeastern, central and southern parts of our country. In addition, Addis Ababa, Jimma, Ilubabor, East Wollega, Guji, West Arsi, West and East Gojjam, North Gondar, Wolaita, Majang, Northwest, South and Southeast Tigray and Gurage zones received light to moderate rainfall, with Bure recording heavy rainfall of 41.5 mm. On the other hand, Melka Jebdu, Mayhanssa, Mehoni, Dire Dawa, Aisha, Chifra, Chefa, Bati, Metema, Semera, Elidar, Awash Arba, Metehara, Dallifage and Kebridahar recorded daytime maximum temperatures ranging from 35.0 to 44.0°C.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በምዕራብ፣ ሰሜን፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ደቡብ፣ ደቡብ ምዕራብ እና በመካከለኛዉ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ ይበልጥ ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ ምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ እና ጌዴኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኢታንግ፣ ኑዌር እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከቤኒሸንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ዋግኸምራ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፣ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ፣ ማዕከላዊና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በጅማ፣ ማዕከላዊ ትግራይ፣ ደቡብ ጎንደር፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ ዞኖች ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ በመልካ ጀብዱ፣ ማይሀንሳ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ፣ መተማ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ከሚሴ፣ ቀብሪደሃር፣ ጭፍራ እና መተሐራ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡
Tomorrow, weather conditions favorable for winter rain will persist, especially over western, northern, northwestern, northeastern, southern, southwest and central parts of the country. In addition, the following zones in Oromia will be particularly affected: Jimma, Ilu-Babor, Buno Bedelle, Horo Guduru, Kellem, East and West Wollega, North, East, Southwest and West Shewa, East and West Hararghe, Arsi and West Arsi, Borena and East Borena, Bale, Guji and West Guji. Addis Ababa; from the Southern Ethiopia region: Wolayita, Gamo, Gofa, Basketo and Gedeo zones; from Sidama region: the zones there; from the Central Ethiopia region: Gurage, East Gurage, Mareqo special zone, Silte, Mu special zone, Hadiya, Halaba, Kembata and Tambaro; from the Southern Nations, Nationalities, and Peoples' Region (Southwest Ethiopia): Keffa, Sheka, Bench Sheko, Konso, West Omo and Dawuro zones; from Gambela: Agnuak, Itang, Nuer and Majang zones; from Benishangul-Gumuz: Assosa, Metekel, Kamashi and Mao Komo zones; from Amhara: West, North, South and Central Gondar, Awi zone, Wag Hemra, North and South Wollo, West and East Gojjam and North Shewa zones; and from Tigray: West, Northwest, East, South, Central and Southeast zones these areas will receive light to moderate rainfall ranging from 1 to 29 mm in many places. Furthermore, heavy rainfall exceeding 30 mm within 24 hours is expected over Jimma, central Tigray, southern Gondar, southwest and west Shewa zones. On the other hand, high daytime temperatures between 35 and 40 degrees Celsius will be recorded in Semera, Elidar, Gambela, Funyido, Abobo, Melka Jebdu, Mayhansa, Mehoni, Dire Dawa, Aisha, Metema, Dallifage, Awash Arba, Kemi’se, Kebridahar, Chifra and Metehara.