Daily Weather Report 26 January 31
Weather Summary for previous day
በትናንትናዉ ዕለት በሰሜን ምስራቅ እና ምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ተስተዉሎባቸዋል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ በቁልቢ እና ጎብየሬ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በምዕራብ እና መካከለኛው ኦሮሚያ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን የነበራቸው ሲሆን በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, the northeast and eastern parts of the country experienced dry, sunny, and windy summer weather. Additionally, the minimum temperature of the day was recorded below 5 degrees Celsius in Kulbi and Gobyere. On the other hand, in some areas of western and central Oromia were cloudy cloud cover, and a few places received rain.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን እና ምስራቅ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ የሚኖራቸው ሲሆን፤ በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች ሆኖ እንደሚመዘገብ የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ በሌላ በኩል በደቡብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ በመካከለኛው እና በሰሜን ምስረቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም የጅማ፣ ጉጂ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ከፋ፣ ቤንችሸኮ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ፣ ጌዲኦ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ እና የሲዳማ ክልል ዞኖች በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡
Tomorrow, the northwest, north, and east parts of the country will experience dry, sunny, and windy Belg weather; and the forecast data indicates that the minimum temperature in some areas will drop below 5 degrees Celsius. On the other hand, there will be cloud cover in the southern, southwest, central, and northeastern areas of the country. Accordingly, in Jimma, Guji, west Arsi, Kefa, Benchsheko, Konta, Dawro, Gedeo, Gamo, Gofa, South Omo, North and South Wollo, and Sidama regions will receive light rain in some areas.