Daily Weather Report 26 January 30

Weather Summary for previous day

Jan. 29, 2026

በትናንትናዉ ዕለት በሰሜን ምስራቅ እና ምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ተስተዉሎባቸዋል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ በጨለንቆ፣ ቁልቢ፣ ጎብየሬ እና በኮረም የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በምዕራብ ኦሮሚያ፣ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ በሲዳማ እና በደቡብ ኢትዮጵያ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡

Yesterday the northeast and eastern regions of the country experienced dry, sunny and windy bega weather. Along with this, the daily minimum temperature was recorded below 5 degrees Celsius in Chelenko, Kulbi, Gobyere and Korum. On the other hand, there was cloud cover over parts of the country in Western Oromia, Central Ethiopia, Sidama, and Southern Ethiopia.

Weather Forecast for next day

Jan. 31, 2026

በነገው ዕለት በሰሜን፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ምስራቅ እና በመካከለኛው የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ይኖራቸዋል፡፡ ከዚህም ጋር በተያያዘም በደቡብ ከፍተኛ ቦታዎች እና በምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች ሆኖ እንደሚመዘገብ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በሌላ በኩል በምዕራብ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ በመሆኑም በጅማ፤ የም ልዩ ዞን እና ከፋ በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡

Tomorrow, the north, northwest, east, and central parts of the country will experience dry, sunny, and windy bega weather. In this regard, numerical forecast indicate that the daily minimum temperature will be recorded below 5 degrees Celsius in the southern highlands and eastern parts of the country. On the other hand, there will be cloud cover over the western and southwestern parts of the country. As a result, Jimma, the Special Zone and Kaffa will experience light rain in a few places.