Daily Weather Report 26 January 29
Weather Summary for previous day
በትናንትናዉ ዕለት በሰሜን፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በሰሜን ምዕራብ፣ በመካከለኛዉ እና በምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ተስተዉሎባቸዋል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ በወገል ጠና፣ በጨለንቆ፣ ቁልብ እና በኮሬም የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በደቡብ፣ በደቡብ ምዕራብ እና በምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ በዳራመሎ፣ እጃጂ፣ ጅማ፣ ሳዉላ፣ አማን፣ ቴርቻ እና ወላይታ ሶዶ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday the northern, north eastern, northwestern, central and eastern regions of the country experienced dry, sunny and windy weather conditions. In addition, the minimum temperature of the day was recorded below 5 degrees Celsius in Wegel Tena, Chelenko, Qulbi and Korem. On the other hand, there was cloud coverage in the southern, southwestern and western regions of the country. In addition, light to moderate rainfall was recorded in Daramelo, Ejaji, Jimma, Saula, Aman, Tercha and Wolaita Sodo.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በሰሜን፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ምስራቅ እና በመካከለኛው የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ይኖራቸዋል፡፡ ከዚህም ጋር በተያያዘም በደቡብ ከፍተኛ ቦታዎች እና በምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች ሆኖ እንደሚመዘገብ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በሌላ በኩል በምዕራብ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ በመሆኑም በጅማ፤ የም ልዩ ዞን እና ከፋ በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡
For tomorrow, the north, northwest, east and central parts of the country will experience dry, sunny and windy Bega’s weather conditions. In this regard, numerical forecast data indicate that the minimum temperature of the day will be recorded below 5 degrees Celsius in the southern highlands and eastern parts of the country. On the other hand, there will be cloud coverage in the western and southwestern parts of the country. Therefore, Jimma; Yem special zone and Kefa will experience light rain in a few places.