Daily Weather Report 26 January 28
Weather Summary for previous day
በትናንትናዉ ዕለት በሰሜን፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በሰሜን ምዕራብ፣ በመካከለኛዉ እና በምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ተስተዉሎባቸዋል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ በጨለንቆ፣ በቁልቢ እና በጅግጅጋ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በደቡብ፣ በደቡብ ምዕራብ እና በምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ በይርጋለም፣ ጋቲራ፣ ሳዉላ፣ አማን፣ ቴርቻ፣ ጅማ፣ አርባምንጭ እና በአንጋቻ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday the weather in the northern, northeast, northwest, central and eastern parts of the country was dry, sunny and windy. In relation to this, minimum temperatures in Chelenko, Kulubi and Jigjiga were recorded below 5 degrees Celsius. Meanwhile, cloudy conditions were observed in the southern, southwest and western parts of the country. Along with this, light to moderate rain was recorded in Yirgaalem, Gatira, Sawula, Aman, Tercha, Jimma, Arba Minch and Angacha.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በሰሜን፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ምስራቅ እና በመካከለኛው የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ይኖራቸዋል፡፡ ከዚህም ጋር በተያያዘም በደቡብ ከፍተኛ ቦታዎች እና በምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች በደጋማ ስፍራዎች ላይ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች ሆኖ እንደሚመዘገብ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በሌላ በኩል በምዕራብ፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በደቡብ ምዕራብና በደቡብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚህም ጋር በተያያዘም የጅማ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች፤ የወላይታ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ደቡብ እና ሰሜን ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡
Tomorrow, the northern, northwestern, eastern and central parts of the country will experience dry, sunny and windy weather. In addition, forecast information indicates that in highland areas of the south and in some eastern parts of the country, minimum temperatures will be recorded below 5 degrees Celsius. Elsewhere, in the western, northeast, southwest and southern areas of the country, cloudy conditions will prevail. In connection with this, light rainfall is expected in some places of the following zones: Jimma, West Arsi, Guji and West Guji zones; Wolayita and Gedeo zones; Gurage, Silte, Hadiya, Halaba, Mareko special zone, Kembata and Tambaro zones; South and North Wollo, North Shewa zones; and parts of the Sidama region.