Daily Weather Report 26 January 27

Weather Summary for previous day

Jan. 26, 2026

በትናንትናው ዕለት በሰሜን፣ በሰሜን ምዕራብ፣ በምስራቅ እና በመካከለኛው የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ የተስተዋለባቸው ሲሆን፤ በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5 ዲግሪ ሴልሽየስ በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በደቡብ ምዕራብ፣ በደቡብ፣ በምዕራብ እና በሰሜን ምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ በሳውላ እና ኢጃጂ ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, dry, sunny, and windy summer weather was observed in the northern, northwestern, eastern, and central parts of our country, with the minimum temperature of the day was recorded below 5 degrees Celsius in a few highland areas of the country. On the other hand, there was cloud cover in the southwestern and western parts of the country. In line with this, light rain was recorded in Sawla and Ejaji.

Weather Forecast for next day

Jan. 28, 2026

በነገው ዕለት በሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ መካከለኛው እና ምስራቅ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ይኖራቸዋል፡፡ ከዚህም ጋር በተያያዘም በጥቂት የምስራቅ አማራ፣ መካከለኛው እና ምስራቅ የሀገሪቱ ደጋማ ስፍራዎች ላይ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች ሆኖ እንደሚመዘገብ የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ በሌላ በኩል በደቡብ ምዕራብና ደቡብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን የሚኖራቸው ሲሆን የጅማ፣ ጉጂ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ከፋ፣ ቤንችሸኮ፣ ዳውሮ፣ ጌዲኦ እና የሲዳማ ክልል ዞኖች በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡

Tomorrow, the North West, North East, Central, and East parts of our country will experience dry, sunny, and windy Bega weather conditions. In association with this, numerical forecast indicates that the minimum temperature of the day will be recorded below 5 degrees Celsius in a few areas of east Amhara, central, and the eastern highlands of the country. On the other hand, there will be cloud cover in the south west, and southern parts of the country. I this regards, in Jimma, Guji, West Arsi, Kefa, Bench Sheko, Dawro, Gedio and Sidama region zones will receive light rain in a few places.