Daily Weather Report 26 January 26

Weather Summary for previous day

Jan. 25, 2026

በትናንትናዉ ዕለት በሰሜን፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛዉ እና በምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ተስተዉሎባቸዋል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ በደባርቅ፣ ወገልጤና፣ አምባ ማርያም፣ ደብረ ብርሃን፣ ቡኢ፣ ቁልቢ፣ ሐሮማያ፣ ኮረም የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች እንዲሁም በጨለንቆ ከዜሮ በታች -1.0 ዲግሪ ሴልሺየስ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በደቡብ፣ በደቡብ ምዕራብ እና በምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን የነበራቸው ሲሆን በጭራ፣ ጅማ፣ ቦሬ፣ ቡርጂ እና ቡሌሆራ ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, the north, northeast, central and eastern regions of the country experienced dry, sunny and windy bega weather. Along with this, in Debark, Wogel Tena, Amba Mariam, Debre Birhan, Bui, Kulbi, Haromaya, Korum the minimum temperature of the day was recorded as 5 degrees Celsius and also in Chelenko minimum temperature was -1.0 degrees Celsius. On the other hand, there was cloud cover in the south, southwest and west of the country, and rain was recorded in Chira, Jimma, Bore, Burji and Bulehora.

Weather Forecast for next day

Jan. 27, 2026

በነገው ዕለት በሰሜን ምስራቅ፣ መካከለኛዉ እና ምስራቅ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ይኖራቸዋል፡፡ ከዚህም ጋር በተያያዘም የምስራቅ አማራ፣ መካከለኛዉ፣ ደቡብ ከፍተኛ ቦታዎች እና ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች በደጋማ ስፍራዎች ላይ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች ሆኖ እንደሚመዘገብ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምዕራብ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ደቡብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን የሚኖራቸዉ ሲሆን በምስራቅ ጎጃም፣ ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ወላይታ፣ ባስኬቶ፣ ጋሞ፣ ጌዴኦ እና በሲዳማ ክልል ዞኖች ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡

Tomorrow, the northeast, central, and eastern regions of our country will experience dry, sunny, and windy bega weather. In this regard, the highlands of eastern Amhara, central, southern, and highlands of the eastern parts of the country the forecast indicates that the minimum daily temperature in the will be recorded below 5 degrees Celsius. On the other hand, there will be cloud cover in the northwest, west, southwest and south of the country, while in the east, Gojjam, West Arsi, Guji and West Guji, Gurage, Silte, Hadiya, Wolaita, Basketo, Gamo, Gedeo and Sidama Region zones will experience light to moderate rainfall.