Daily Weather Report 26 January 25
Weather Summary for previous day
በትናንትናዉ ዕለት በሰሜን፣ በመካከለኛዉ፣ ሰሜን ምስራቅ እና በምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ተስተዉሎባቸዋል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ በዳንግላ እና በኤምዲቢር የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በደቡብ፣ በደቡብ ምዕራብ እና በምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡
Yesterday the weather was dry, sunny and windy in the northern, central, northeast and eastern parts of the country. In addition, daytime low temperatures were recorded below 5 degrees Celsius in Dangila and Emdibir. On the other hand, the southern, southwest and western parts of the country were cloudy.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በሰሜን፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ምስራቅ እና በመካከለኛው የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ይኖራቸዋል፡፡ ከዚህም ጋር በተያያዘም በሰሜን ምስራቅ፣ በደቡብ ከፍተኛ ቦታዎች እና በምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች በደጋማ ስፍራዎች ላይ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች ሆኖ እንደሚመዘገብ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በሌላ በኩል በምዕራብ፣ መካከለኛዉ፣ ደቡብ ምዕራብና ደቡብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚህም ጋር በተያያዘም የደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ጅማ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ እና ቦረና ዞኖች፤ የወላይታ፣ ጋሞ፣ ቡርጅ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ቀበና ልዩ ዞን፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡
Tomorrow the weather will be dry, sunny and windy in the north, northeast, northwest, east and central parts of the country. In addition, forecast information indicates that daytime low temperatures in northeastern areas, highland locations in the south, and eastern parts of the country in some places will drop below 5 degrees Celsius. Elsewhere, cloudiness will prevail over the west, central, southwest and southern parts of the country. Accordingly, light to moderate rainfall is expected in a few places of the following zones: South West Shewa, Jimma, Arsi and West Arsi, Guji and West Guji, Bale and Borena; Wolayita, Gamo, Burji and Gedeo; zones of Gurage, Silte, Kebena special zone,Mareko special zone,Hadiya,Halaba,Yem special zone, Kembata and Tambaro and the Sidama region.