Daily Weather Report 26 January 24
Weather Summary for previous day
በትናንትናዉ ዕለት በሰሜን፣ በመካከለኛዉ እና በምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ተስተዉሎባቸዋል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ በቡኢ፣ ጨለንቆ እና በቁልቢ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በደቡብ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ በደቡብ ምዕራብ እና በምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ በሸንዲ፣ ወገልጤና፣ ጉቤቲ፣ ጋሳየ እና በመርጦ ለማርያም ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday the weather was dry, sunny and windy in the northern, central and eastern parts of the country. In connection with this, the daytime low temperatures in Bu’i, Chelenko and Kulubi were recorded below 5 degrees Celsius. On the other hand, cloudy skies were observed in the southern, northeastern, southwestern and western parts of the country. Along with that, light rain was recorded in Shindi, Wegeltena, Gubeti, Gasay and Merto LeMariam.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በሰሜን፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ምስራቅ እና በመካከለኛው የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ይኖራቸዋል፡፡ ከዚህም ጋር በተያያዘም በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛዉ፣ በደቡብ ከፍተኛ ቦታዎች እና በምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች በደጋማ ስፍራዎች ላይ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች ሆኖ እንደሚመዘገብ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በሌላ በኩል በምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ደቡብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን የሚኖራቸው ሲሆን በምዕራብ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ደቡብ ወሎ እና የሲዳማ ክልል ዞኖች በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡
Tomorrow the weather will be dry, sunny and windy in the north, northeast, northwest, east and central parts of the country. In addition, forecast information indicates that daytime minimum temperatures in parts of the northeast, central highlands, southern highlands and eastern regions will drop to below 5 degrees Celsius. On the other hand, cloudy conditions are expected in the west, southwest and southern areas of the country, and light rain will fall in a few places in western Arsi, Guji and western Guji, southern Wollo and the Sidama zones.