Daily Weather Report 26 January 23

Weather Summary for previous day

Jan. 22, 2026

በትናንትናዉ ዕለት በሰሜን፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛዉ እና በምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ተስተዉሎባቸዋል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ በአምባ ማርያም፣ ቡኢ፣ አርሲ ሮቤ፣ ጨለንቆ፣ ሐሮማያ፣ ቁልቢ እና በኮረም የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በደቡብ፣ በደቡብ ምዕራብ እና በምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን የነበራቸው ሲሆን በጋቲራ ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday the northern, northeastern, central and eastern regions of the country experienced dry, sunny and windy bega weather. In addition, the daily minimum temperature was recorded below 5 degrees Celsius in Amba Mariam, Bui, Arsi Robe, Chelenko, Haromaya, Kulbi and Korum. On the other hand, there was cloud cover over the southern, southwestern, and western parts of the country, with rainfall recorded in Gatira.

Weather Forecast for next day

Jan. 24, 2026

በነገው ዕለት በሰሜን፣ ሰሜን ምስራቅ፣ መካከለኛዉ እና ምስራቅ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ይኖራቸዋል፡፡ ከዚህም ጋር በተያያዘም የምስራቅ አማራ፣ መካከለኛዉ፣ ደቡብ ከፍተኛ ቦታዎች እና ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች በደጋማ ስፍራዎች ላይ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች ሆኖ እንደሚመዘገብ የትንበያ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምዕራብ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ደቡብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን የሚኖራቸዉ ሲሆን በጥቂት የባህር ዳር ዙርያ፣ ጅማ፣ ሸካ፣ ከፋ እና ጌዴኦ ዞኖች ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡

Tomorrow, the North, Northeast, Central, and East regions of our country will experience dry, sunny, and windy Bega weather. In this regard, East Amhara, in the highlands of the central, southern, and eastern parts of the country forecast indicate that the daily minimum temperature will be recorded below 5 degrees Celsius. On the other hand, there will be cloud cover over the northwest, west, southwest and south of the country, with light rain expected in some Bahir Dar zuriya, Jimma, Sheka, Kefa and Gedeo zones.