Daily Weather Report 26 January 22
Weather Summary for previous day
በትናንትናዉ ዕለት በሰሜን፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛዉ እና በምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ተስተዉሎባቸዋል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ በዓለም ከተማ፣ ሐሮማያ፣ ቁሉቢ፣ ጨለንቆ፣ ቡኢ እና ጅግጅጋ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በደቡብ፣ በደቡብ ምዕራብ እና በምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ ባህር ዳር፣ በደሌ፣ ጨዋቃ፣ ጎሬ፣ቡሬ፣ማሸ፣ኦቦመርጋ፣ ኮሶበር እና በሽንዲ ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday the northern, north-eastern, central and eastern regions of the country experienced dry, sunny and windy bega’s weather. In addition, the lowest daily temperature was recorded below 5 degrees Celsius in Al-Ata, Haromaya, Qulbi, Chelenko, Bui and Jigjiga. On the other hand, there was cloud coverage in the southern, southwestern and western regions of the country. In addition, rain was recorded in Bahir Dar, Bedele, Chewaka, Gore, Bure, Masha, Obomerga, Kosober and Shindi.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ሰሜን ምስራቅ፣ መካከለኛዉ እና ምስራቅ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ይኖራቸዋል፡፡ ከዚህም ጋር በተያያዘም የምስራቅ አማራ፣ መካከለኛዉ፣ ደቡብ ከፍተኛ ቦታዎች እና ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች በደጋማ ስፍራዎች ላይ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች ሆኖ እንደሚመዘገብ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ በሌላ በኩል በምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ደቡብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን የሚኖራቸዉ ሲሆን፣ በጅማ፣ ሸካ እና ከፋ ዞኖች ላይ በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡
For tomorrow, the northwest, north, northeast, central and eastern parts of our country will experience dry, sunny and windy bega’s weather conditions. In this regard, numerical forecast data indicates that the minimum temperature of the day will be recorded below 5 degrees Celsius in the highlands of East Amhara, central, southern highlands and eastern parts of the country. On the other hand, there will be cloud coverage in the west, southwest and south of the country, and light rain will be experienced in a few places in Jimma, Sheka and Kefa zones