Daily Weather Report 26 January 21
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በሰሜን ምዕራብ፣ በሰሜን እና በምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ተስተውሎባቸዋል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ በአምባማርያም፣ ሐሮማያ፣ ቁሉቢ፣ ከረም፣ ጎሮበቀርሳ እና ጅግጅጋ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው፣ በደቡብ፣ በደቡብ ምዕራብ እና በምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ በደብረ ታቦር፣ መካነሰላም፣ ላይበር፣ አይከል፣ አርጆ እና በሸንዲ ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, the weather in the country’s northwest, north and east was dry, sunny and windy. At the same time, places such as Ambamariam, Haromaya, Kulubi, Korem, Gorobekersa and Jigjiga recorded daily low temperatures below 5 degrees Celsius. Meanwhile, cloudy conditions were observed in the northeast, central, south, southwest and west parts of the country. In line with this, Debre Tabor, Mekane Selam, Laiber, Aykel, Arjo and Shindi recorded rainfall.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በሰሜን፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በሰሜን ምዕራብ፣ በምስራቅ፣ በደቡብ ደጋማ ስፍራዎች እና በመካከለኛው የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ የሚስተዋል ሲሆን፤ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች ሆኖ የሚመዘገብ ሲሆንና፤ የሌሊትና የማለዳው ቅዝዝቃዜም እንደሚኖረው የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ በሌላ በኩል በምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ደቡብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን የሚኖራቸው ሲሆን ኢሉባቦር፣ ጅማ፣ ቡኖበደሌ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ቤንችሸኮ፣ ዳውሮ፣ የም እና ከምባታ ዞኖች እና የሲዳማ ክልል ዞኖች በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡
Tomorrow, dry, sunny and windy conditions are expected in the north, northeast, northwest, east, southern lowlands and central parts of the country. Daytime low temperatures will be below 5°C, and forecasts also indicate frost during the night and early morning. Meanwhile, cloudy skies with light rainfall are expected in parts of the west, southwest and south including small areas of Iluababora,Jimma,Buno Bedelle,Sheka,Kefa,Bench Sheko,Dawuro,Yem and Kembata zones, as well as zones of the Sidama region.