Daily Weather Report 26 January 20
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በሰሜን ምዕራብ፣ በምስራቅ እና በመካከለኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ተስተውሎባቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በጥቂት ደጋማ ስፍራዎች ላይ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5 ዲግሪ ሴልሽየስ በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በደቡብ ምዕራብ፣ በደቡብ፣ በምዕራብ እና በሰሜን ምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ በእምድብር፣ ወላይታሶዶ፣ ሳውላ፣ አርባምንጭ፣ ይርጋለም፣ ወንዶገነት እና ላሊበላ ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, the North West, North East, Central, and East parts of our country experienced dry, sunny, and windy Bega weather. In this regard, the minimum temperature of the day was recorded below 5 degrees Celsius in a few highland areas of the country. On the other hand, there was cloud cover in the southwestern and western parts of the country. In line with this, light rain was recorded in Emdibir, Sawla, Wolaitasodo, Ariba Minch, Yirgalem, Wondogenet and Yirgalem.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ መካከለኛው እና ምስራቅ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ይኖራቸዋል፡፡ ከዚህም ጋር በተያያዘም በጥቂት የምስራቅ አማራ፣ መካከለኛው፣ ደቡብ ከፍተኛ ቦታዎች እና ምስራቅ የሀገሪቱ ደጋማ ስፍራዎች ላይ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች ሆኖ እንደሚመዘገብ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ በሌላ በኩል በምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ደቡብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን የሚኖራቸው ሲሆን የኢሉባቦር፣ ጅማ፣ ቡኖበደሌ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ቤንችሸኮ፣ ዳውሮ እና ኮንታ ዞኖች በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡
Tomorrow, the North West, North East, Central, and East parts of our country will experience dry, sunny, and windy Bega weather conditions. In association with this, numerical forecast indicates that the minimum temperature of the day will be recorded below 5 degrees Celsius in a few areas of east Amhara, central, south highlands, and the eastern highlands of the country. On the other hand, there will be cloud cover in the west, south west, and southern parts of the country, in Ilubabor, Jimma, Bunobedele, Sheka, Kefa, Benchsheko, Konta and Dawro zones will receive light rain in a few places.