Daily Weather Report 26 January 18
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በአብዛኛው የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ አመዝኖባቸው ውሏል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ በጥቂት የሀገሪቱ ደጋማ ስፍራዎች ላይ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5 ዲግሪ ሴልሽየስ በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በደቡብ ምዕራብ እና ምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን የነበራቸው ሲሆን በጎሬ ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, most parts of the country experienced dry, sunny, and windy summer weather. In this regard, the minimum temperature of the day was recorded below 5 degrees Celsius in a few highlands of the country. On the other hand, there was cloud coverage in the southwestern and western parts of the country, and rain was recorded in Gore.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በሰሜን፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ መካከለኛው እና ምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ይስተዋልባቸዋል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ በጥቂት የምስራቅ አማራ፣ መካከለኛው፣ ደቡብ ከፍተኛ ቦታዎች፣ ምስራቅ ኦሮሚያ እና ምስራቅ የሀገሪቱ ደጋማ ስፍራዎች ላይ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች ሆኖ እንደሚመዘገብ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በሌላ በኩል በምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ደቡብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን የሚኖራቸው ሲሆን የጅማ፣ ጉጂ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ከፋ፣ ሀድያ፣ ከምባታ፣ ወላይታ፣ ጌዲኦ ዞኖች እና የሲዳማ ክልል ዞኖች በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡
Tomorrow, the north, north west, north east, central, and east parts of our country will experience dry, sunny, and windy Bega weather conditions. In this respect, numerical forecast indicates that the minimum temperature of the day will be recorded below 5 degrees Celsius in a few areas of east Amhara, central, south highlands, east Oromia, and the eastern highlands of the country. On the other hand, there will be cloud coverage in the west, south west, and south areas of the country; with Jimma, Guji, west Arsi, Kefa, Hadiya, Kembata, Walaita, Gedeo zones, and Sidama region zones will receive light rain in a few areas.