Daily Weather Report 26 January 17
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በአብዛኛው የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ተስተዉሎባቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ በወገልጤና፣ አለምከተማ፣ ቢሾፍቱ፣ ቡኢ፣ ጨለንቆ እና ቁሉቢ ላይ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5 ዲግሪ በታች ሴልሽየስ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በደቡብ ምዕራብ እና ምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ አልፎ አልፎ የደመና ሽፋን የነበራቸው፡፡
Yesterday, most parts of the country experienced dry, sunny, and windy Bega weather. In this regard, the minimum temperature of the day was recorded below 5 degrees Celsius in Wegeltena, Alemketema, Bishoftu, Bui, Chelenk,o and Kulubi. On the other hand, there was occasional cloud coverage in the southwestern and western parts of the country.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በሰሜን ምዕራብ፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው እና በምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ይኖራቸዋል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ በጥቂት የሀገሪቱ ደጋማ ስፍራዎች ላይ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5°C በታች እንደሚሆን የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በሌላ በኩል በምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ እና ደቡብ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን የሚኖራቸው ሲሆን፤ ከዚሁ ጋር በተያያዘም የጉጂ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ሀድያ፣ ከምባታ፣ ጌድኦ እና የሲዳማ ክልል ዞኖች በጥቂት ቦታዎቻቸው ላይ አነስተኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡
For the upcoming day, the northwest, northeast, central, and eastern parts of the country will experience dry, sunny, and windy Bega weather conditions. Associated with this, forecast information indicates that the minimum temperature of the day will be below 5°C in a few highlands of the country. On the other hand, there will be cloud cover over the western, southwestern, and southern parts of our country, and in this regard, Guji, west Arsi, Hadiya, Kembata, Gedeo, and Sidama region zones will receive light rain at a few places.