Daily Weather Report 26 January 16
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በአብዛኛው የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በኮረም፣ ጋሸና፣ ወገልጤና፣ አምባማሪያም፣ ደባርቅ፣ ጉዶበረት፣ ቢሾፍቱ፣ ቡኢ፣ እምድብር፣ ጅማ፣ ባሌሮቤ፣ ሐሮማያ፣ ቁሉቢ እና ጅግጅጋ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ 5 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች እንዲሁም በጨለንቆ ከዜሮ በታች -1.0 ዲግሪ ሴልሺየስ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በጥቂት የደቡብ ምዕራብ እና ምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡
Yesterday, dry, sunny, and windy Bega-season weather conditions prevailed over most parts of the country. In this regards, the daily minimum temperatures below 5 °C were recorded in Korem, Gashena, Wegeltena, Amba Mariyam, Debark, Gundoberet, Bishoftu, Bui, Emdibir, Jimma, Bale Robe, Haromaya, Kulubi, and Jijiga while in Chelenko the daily minimum temperature was recorded -1.0°C, which is below zero. On the other hand, there was cloud cover over the Southwestern and Western parts of our country.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በሰሜን ምስራቅ፣ መካከለኛው እና ምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ የሚኖራቸው ሲሆንና፤ በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ ደግሞ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ 5 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች ሆኖ እንደሚመዘገብ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ በሌላ በኩል በጥቂት የደቡብ፣ ደቡብ ምዕራብ እና ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጎፋ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከኦሮሚያ ክልል የጉጂ እና ጅማ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ ዞን በጥቂት ቦታዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡
Tomorrow, dry, sunny, and windy Bega-season weather conditions are expected to prevail over the northeastern, central, and eastern parts of the country, and in a few places, the daily maximum temperature will drop below 5°C. On the other hand, there will be cloud cover over the southern, southwestern, and western parts of the country. In this regards, light rain will receive in a few places of southern Ethiopia region Gofa, South Omo, and Gedio zones; the Sidama region zones; from Oromia region Guji and Jimma zones; and from southwestern Ethiopia the Kefa zone.