Daily Weather Report 26 January 15
Weather Summary for previous day
በትናንትናዉ ዕለት በአብዛኛዉ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ተስተዉሎባቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በአዲግራት፣ ማይጨዉ፣ ውቅሮ፣ አድዋ፣ ወገልጤና፣ አምባ ማርያም፣ ባቲ፣ መሀል ሜዳ፣ አለም ከተማ፣ ወረ ኢሉ፣ ቢሾፍቱ፣ መልካ ጀብዱ፣ ጨፌዶንሳ፣ ቡኢ፣ ባሌ ሮቤ፣ ጅማ፣ ጎብይሬ፣ ጅግጅጋ፣ ቁልቢ እና አርሲ ሮቤ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ 5 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች፣ እንዲሁም በጨለንቆ ከዜሮ በታች -3.0 ዲግሪ ሴልሺየስ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በጥቂት የደቡብ ምዕራብ እና ምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡
Yesterday, most parts of the country experienced dry, sunny and windy summer weather. In this regard, in Adigrat, Maichew, Wukro, Adwa, Wegeltena, Amba Mariam, Bati, Mehal Meda, Alem Ketema, Were Ilu, Bishoftu, Melka Jebdu, Chefedonsa, Bui, Bale Robe, Jimma, Gobeyere, Jigjiga, Qulbi and Arsi Robe, the minimum temperature of the day was recorded as below 5 degrees Celsius, while in Chelenko it was below zero -3.0 degrees Celsius. On the other hand, there was cloud cover in some parts of the southwest and west of the country.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው እና በምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ይስተዋልባቸዋል፡፡ከዚህም ጋር ተያይዞ በማይጨዉ፣ ቁሉብ፣ ዉቅሮ፣ ደብረ ታቦር፣ ወገልጤና፣ አምባ ማርያም፣ ኮምቦልቻ፣ መሀል መዳ፣ ባቲ፣ አለም ከተማ፣ ደብረ ብርሃን፣ ቢሾፍቱ፣ ቡኢ፣ ባሌ ሮቤ፣ ጅግጅጋ እና ጋሸና የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች እንደሚሆንና የሌሊቱና የማለዳዉ ቅዝቃዜ ቀጣይነት እንደሚኖረው የትንበያ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ በሌላ በኩል በጥቂት የደቡብ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡
Tomorrow, the northeast, central and eastern parts of the country will experience dry, sunny and windy summer weather. In addition, the minimum temperature in Maichew, Qulbi, Wukro, Debre Tabor, Wegel Tena, Amba Mariam, Kombolcha, Mehal Meda, Bati, Alem Ketema, Debre Birhan, Bishoftu, Bui, Bale Robe, Jigjiga and Gashena will be below 5 degrees Celsius and the night and morning cold will continue. On the other hand, there will be cloud cover in some parts of the south and southwest of the country.