Daily Weather Report 26 January 14

Weather Summary for previous day

Jan. 13, 2026

በትናንትናው ዕለት በአብዛኛው የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ተስተውሎባቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በአዲግራት፣ ማይጨው፣ ውቅሮ፣ አጽቢ፣ አይደር፣ ዳንግላ፣ ደብረ ታቦር፣ ወገልጤና፣ አምባ ማርያም፣ ኮምቦልቻ፣ ባቲ፣ መሃል ሜዳ፣ አለም ከተማ፣ ደብረ ብርሃን፣ ጋሸና፣ ጉበቲ፣ ቢሾፍቱ፣ ጨፌዶንሳ፣ ቡኢ፣ ባሌሮቤ፣ ቦሬ፣ ጎብየሬ፣ ጅግጅጋ፣ ቁልቢ እና መልካ ጀብዱ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ 5 ዲግሪ በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ በተጨማሪም በጨለንቆ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከዜሮ በታች -3.0 ዲግሪ ሴልሽ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በጥቂት የደቡብ ምዕራብ እና ምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡

Yesterday, dry, sunny and windy summer weather was observed in most parts of the country. In this regard, in Adigrat, Maychew, Wukro, Atsbi, Ayder, Dangla, Debre Tabor, Wogeltiye, Amba Mariam, Kombolcha, Bati, Mahle Meda, Alem Ketema, Debre Birhan, Gashena, Gubeti, Bishoftu, Chefedonsa, Bui, Balerobe, Bore, Gobyere, Jigjiga, Qulbi and Melka Jebdu recorded the lowest temperature of the day at 5 degrees Celsius. In addition, the lowest temperature of the day was recorded at -3.0 degrees Celsius in Chelenko. On the other hand, there was cloud cover in some parts of the southwestern and western parts of the country.

Weather Forecast for next day

Jan. 15, 2026

በነገዉ ዕለት በሰሜን ምስራቅ፣ በሰሜን፣ በመካከለኛው፣ በደቡብ ከፍተኛ ቦታዎች እና በምስራቅ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ይኖራቸዋል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ በአዲግራት፣ ማይጨዉ፣ ደብረብርሀን፣ አለም ከተማ፣ ሾላገበያ፣ እንዋሪ፣ መሀልሜዳ፣ አምባማርያም፣ ባቲ፣ ወገልጤና፣ ቡኢ፣ እምድብር፣ ቢሾፍቱ፣ አርሲ ሮቤ፣ ቦሬ፣ ባሌ ሮቤ፣ ሐሮማያ፣ ቁሉቢ እና ጅግጅጋ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች እንደሚሆንና የሌሊት እና የማለዳዉ ቅዝቃዜ ቀጣይነት እንደሚኖረው የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ በሌላ በኩል በጥቂት በምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡

Tomorrow, the northeast, north, central, southern highlands, and eastern parts of our country will experience dry, sunny, and windy summer weather. Along with this, there will be rain in Adigrat, Maychew, Debre Birhan, Alem Ketema, Shola Gebeya, Enwari, Mehalmeda, Ambamariam, Bati, Wogeltiye, Bui, Emdbir, Bishoftu, Arsi Robe, Bore, Bale Robe, Haromaya, Kulbi and Jigjiga Forecast indicates that the minimum temperature of the day will be below 5 degrees Celsius in, and that the night and morning cold will continue. On the other hand, there will be cloud cover in a few western areas of our country.