Daily Weather Report 26 January 13

Weather Summary for previous day

Jan. 12, 2026

በትናንትናው ዕለት በአብዛኛው የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ተስተውሎባቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በወገልጠና፣ ባቲ፣ አለምከተማ፣ ደብረብርሀን፣ ቢሾፍቱ፣ ቡኢ፣ አርሲሮቤ፣ ባሌሮቤ፣ ሐሮማያ፣ ቁሉቢ፣ ጅግጅጋ እና መልካጀብዱ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ 5 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች እንዲሁም ጨለንቆ ከዜሮ በታች -2.0 ዲግሪ ሴልሺየስ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በጥቂት የደቡብ ምዕራብ እና በምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን የነበራቸው ሲሆን በቴፒ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, dry, sunny, and windy Bega-season weather conditions prevailed over most parts of the country. In this regards, the daily minimum temperatures below 5 °C were recorded in Wegeltena, Bati, Alemketama, Debre Birhan, Bishoftu, Bui, Arsi Robe, Bale Robe, Haromaya, Kulubi, Jijiga and Melka Jebdu, while in Chelenko the daily minimum temperature was recorded −2.0°C, which is below zero. On the other hand, there was cloud cover over the Southwestern and Western parts of our country, while light rain was recorded in Tepi.

Weather Forecast for next day

Jan. 14, 2026

በነገዉ ዕለት በሰሜን ምስራቅ፣ በሰሜን፣ በመካከለኛ፣ በደቡብ ከፍተኛ ቦታዎች እና በምስራቅ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ይኖራቸዋል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ በአዲግራት፣ ማይጨዉ፣ ደብረብርሀን፣ ሾላገበያ፣ እንዋሪ፣ መሀልሜዳ፣ አምባማርያም፣ ባቲ፣ ወገልጤና፣ ቡኢ፣ እምድብር፣ ቢሾፍቱ፣ አርሲ ሮቤ፣ ባሌ ሮቤ፣ ሐሮማያ፣ ቁሉቢ፣ ጨለንቆ እና ጅግጅጋ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች እንደሚሆንና የሌሊት እና የማለዳዉ ቅዝቃዜም ቀጣይነት እንደሚኖረው የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ በሌላ በኩል በጥቂት የደቡብ ምዕራብ እና በምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡

Tomorrow, dry, sunny, and windy Bega-season weather conditions are expected to prevail over the northeastern, north, central, southern highland, and eastern parts of the country. In this regard, in Adigrat, Maichew, Debark, Debre Birhan, Shola Gebeya, Enwari, Mehal Meda, Amba Mariyam, Bati, Wegeltena, Bui, Emdibir, Bishoftu, Arsi Robe, Bale Robe, Haromaya, Kulubi, Chelenko, and Jigjiga the daily minimum temperature will drop below 5 °C, and nighttime and early-morning cold conditions will persist. On the other hand, there will be cloud cover over the southwestern and western parts of the country.