Daily Weather Report 26 January 12

Weather Summary for previous day

Jan. 11, 2026

በትናንትናው ዕለት በሰሜን፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው፣ በደቡብ ደጋማ ስፍራዎች እና በምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ተስተዉሎባቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በባቲ፣ አለምከተማ፣ ጋሸና፣ ቢሾፍቱ፣ ቡኢ፣ በባሌሮቤ፣ ቦሬ፣ ቁሉቢ፣ ሐሮማያ እና ጅግጅጋ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5°C በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በምዕራብና ደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ ሳሳ ያለ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡

Yesterday, the northern, northeastern, central, southern highlands, and eastern parts of the country experienced dry, sunny, and windy Bega weather. In this regard, the minimum temperature of the day was recorded below 5°C in Bati, Alemketama, Gashena, Bishoftu, Bui, Balerobe, Bore, Kulubi, Haromaya, and Jigjiga. Conversely, there was light cloud coverage over the western and southwestern parts of the country.

Weather Forecast for next day

Jan. 13, 2026

በነገው ዕለት በአብዛኛው የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ይኖራቸዋል፡፡ ስለሆነም በአዲግራት፣ ማይጨው፣ ኮረም፣ ደባርቅ፣ ዳንግላ፣ ወገልጤና፣ ጋሸና፣ አምባማሪያም፣ መሀልሜዳ፣ ባቲ፣ አለምከተማ፣ ደብረብርሀን፣ ሾላገበያ፣ ቢሾፍቱ፣ ቡኢ፣ አርሲሮቤ፣ ባሌሮቤ፣ ጨለንቆ፣ ቁሉቢ፣ ሐሮማያ እና ጅግጅጋ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5°C በታች እንደሚሆንና የሌሊት እና የማለደው ቅዝቃዜ በተመሳሳይ ሁኔታ እንደሚቀጥል የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በሌላ በኩል በጥቂት የደቡብ ምዕራብና ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡

For the upcoming day, the Bega dry, sunny, and windy weather conditions will prevail in most parts of our country. According to the forecast information, the daily minimum temperature may drop below 5°C in Adigrat, Maichew, Korem, Debark, Dangila, Wegeltena, Gashena, Ambamariam, Mehalmeda, Bati, Alemketema, Debrebrehan, Sholagebeya, Bishoftu, Bui, Arsirobe, Balerobe, Chelenko, Kulubi, Haromaya, and Jigjiga, with cold conditions persisting in the same manner during early morning and night will continue in the same conditions. However, there will be cloud coverage in a few southwestern and western parts of the country.