Daily Weather Report 26 January 11
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በአብዛኛው የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ተስተውሎባቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በዳንግላ፣ ባቲ፣ አለምከተማ፣ ቢሾፍቱ፣ ቡኢ፣ አርሲሮቤ፣ ባሌሮቤ፣ ቁሉቢ እና መልካጀብዱ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ 5 ዲግሪ በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በጥቂት የደቡብ ምዕራብ እና በደቡብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡
Yesterday, dry, sunny, and windy Bega-season weather conditions prevailed over most parts of the country. In association with this, the daily minimum temperatures below 5 °C were recorded in Dangla, Bati, Alem Ketema, Bishoftu, Bui, Arsi Robe, Bale Robe, Kulubi, and Melka Jebdu. On the other hand, cloud cover was observed over a few areas in the southwestern and southern parts of the country.
Weather Forecast for next day
በነገዉ ዕለት የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማው የአየር ሁኔታ በሰሜን ምዕራብ፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛ፣ በደቡብ ከፍተኛ ቦታዎች እና በምስራቅ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ ይስተዋላል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በማይጨዉ፣ አድግራት፣ ደባርቅ፣ ደብረብርሀን፣ ሾላገበያ፣ እንዋሪ፣ መሀልሜዳ፣ አምባማርያም፣ ባቲ፣ ወገልጤና፣ ቡኢ፣ እምድብር፣ ቢሾፍቱ፣ አርሲ ሮቤ፣ ባሌ ሮቤ፣ ሐሮማያ፣ ቁሉቢ፣ ጨለንቆ እና ጅግጅጋ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች እንደሚሆንና የሌሊት እና የማለዳዉ ቅዝቃዜም ቀጣይነት እንደሚኖረው አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በሌላ በኩል በደቡብ፣ ደቡብ ምዕራብ እና በምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ አልፎ አልፎ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡
Tomorrow, the dry, sunny, and windy Bega-season weather conditions are expected to prevail over the northwestern, northeastern, central, southern highland, and eastern parts of the country. In association with this, numerical forecast indicate that in Maichew, Adigrat, Debark, Debre Birhan, Shola Gebeya, Enewari, Mehal Meda, Amba Mariyam, Bati, Wegeltena, Bui, Emdibir, Bishoftu, Arsi Robe, Bale Robe, Haromaya, Kulubi, Chelenko, and Jigjiga, the daily minimum temperature will drop below 5 °C, and nighttime and early-morning cold conditions will persist. On the other hand, there will be occasional cloud cover over the southern, southwestern, and western parts of the country.