Daily Weather Report 26 January 09

Weather Summary for previous day

Jan. 8, 2026

በትናንትናው ዕለት በአብዛኛው የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ተስተውሎባቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በአዲግራት፣ ማይጨው፣ ውቅሮ፣ ኮረም፣ ዳንግላ፣ ባህርዳር፣ ወገልጤና፣ ጋሸና፣ መሀልመዳ፣ ደብረብርሀን፣ ቢሾፍቱ፣ ቡኢ፣ አርሲሮቤ፣ ባሌሮቤ፣ ቁሉቢ፣ ሐሮማያ እና ጨፌዶንሳ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ 5 ዲግሪ በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ በተጨማሪም በጨለንቆ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት ከዜሮ በታች -3.0 ዲግሪ ሴልሽ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በደቡብ ምዕራብ እና በምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ አልፎ አልፎ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡

Yesterday, most parts of the country experienced dry, sunny, and windy weather. In this regard, in Adigrat, Maichew, Wukro, Korem, Dangla, Bahir Dar, Wegeltena, Gashena, Mehalmeda, Debre Berhan, Bishoftu, Bui, Arsi Robe, Bale Robe, Kulubi, Haramaya, and Chefedonsa the daily minimum temperature was recorded below 5 degrees Celsius. Additionally, in Chelenko the daily minimum temperature was recorded -3.0 °C. On the other hand, there was occasional cloud cover in the southwest and western parts of the country.

Weather Forecast for next day

Jan. 10, 2026

በነገዉ ዕለት በሰሜን ምስራቅ፣ በሰሜን፣ በመካከለኛ፣ በደቡብ ከፍተኛ ቦታዎች እና በምስራቅ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ይስተዋልባቸዋል፡፡ በመሆኑም በማይጨዉ፣ አድግራት፣ ደባርቅ፣ ደብረብርሀን፣ ሾላገበያ፣ እንዋሪ፣ መሀልሜዳ፣ አምባማርያም፣ ባቲ፣ ወገልጤና፣ ቡኢ እንድብር፣ ቢሾፍቱ፣ አርሲ ሮቤ፣ ባሌ ሮቤ፣ ሐሮማያ፣ ቁሉቢ፣ ጨለንቆ እና ጅግጅጋ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች እንደሚሆንና የሌሊት እና የማለዳዉ ቅዝቃዜም ቀጣይነት እንደሚኖረው አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በሌላ በኩል በደቡብ፣ ደቡብ ምዕራብ እና በምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ አልፎ አልፎ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡

Tomorrow, dry, sunny, and windy Bega-season weather conditions are expected to prevail over the northeastern, northern, central, southern highland, and eastern parts of the country. Accordingly, in Maichew, Adigrat, Debark, Debre Birhan, Shola Gebeya, Enwari, Mehal Meda, Amba Mariyam, Bati, Wegeltena, Bui Endibir, Bishoftu, Arsi Robe, Bale Robe, Haromaya, Kulubi, Chelenko, and Jigjiga the daily minimum temperature will drop below 5 °C, and numerical weather forecast indicates that nighttime and early-morning cold conditions will persist. On the other hand, there will be cloud cover over the southern, southwestern, and western parts of the country.