Daily Weather Report 26 January 08

Weather Summary for previous day

Jan. 7, 2026

በትናንትናው ዕለት በአብዛኛው የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ አመዝኖባቸው ውሏል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ በደባርቅ፣አዲግራት ፣ ማይጮ፣ ቢሾፍቱ፣ ጅማ፣ ባሌ ሮቤ፣ አለም ከተማ፣ ቁሉቢ፣ አይደር፣ በደብረብርሀን እና ጨፌዶንሳ ላይ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ 5 ዲግሪ በታች እና -ጨለንቆ -2.0 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በጥቂት የደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን የነበራቸው ሲሆን በጎሬ ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, most parts of the country experienced dry, sunny and windy summer weather. In this regard, the minimum temperature of the day was recorded as below 5 degrees Celsius in Debarq, Adigrat, Maicho, Bishoftu, Jimma, Bale Robe, Alem Ketema, Qulubi, Ayder, Debre Birhan and Chefedonsa. On the other hand, there was cloud cover in some parts of the southwestern part of the country and rain was recorded in Gore.

Weather Forecast for next day

Jan. 9, 2026

በነገው ዕለት በሰሜን፣ ምዕራብ፣ መካከለኛው እና ምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በሰሜን ምስራቅ፣ መካከለኛው፣ ደቡብ ከፍተኛ ቦታዎች እና ምስራቅ የሀገርቱ ክፍሎች በደጋማ ስፍራዎቻቸዉ ላይ የለሊቱና የማለዳዉ ቅዝቃዜ እንደሚጨምርና የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5 ዲግሪ ሴልሽየስ በታች ሆኖ እንደሚመዘገብ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ በደቡብ ምዕራብ እና ደቡብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል ፡፡

Tomorrow, the northwest, northeast, central, and east parts of our country will experience dry, sunny, and windy Bega weather. In line with this, numerical forecast information indicates that in north east, central, south highlands, and eastern parts of the country the night and early morning coldness will increase over their highlands and the minimum temperature of the day will be recorded below 5 degrees Celsius. On the other hand, there will be cloud coverage in the south west parts of the country.