Daily Weather Report 26 January 05

Weather Summary for previous day

Jan. 4, 2026

በትናንትናው ዕለት በአብዛኛው የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ አመዝኖባቸው ውሏል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ በደባርቅ፣ ዳንግላ፣ መሀልመዳ፣ ቢሾፍቱ፣ ቡኢ፣ ባሌሮቤ፣ ሚኤሶ፣ ቁሉቢ፣ ጋሸና እና ጨፌዶንሳ ላይ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ 5 ዲግሪ በታች እና በደብረብርሀን -0.4፣ ጨለንቆ -4.0 እና ሐሮማያ -3.4 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በጥቂት የደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን የነበራቸው ሲሆን በአማን ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, most parts of the country experienced dry, sunny, and windy Bega weather. In this regard, the minimum temperature of the day was recorded below 5 degrees Celsius in Debark, Dangila, Mehalmeda, Bishoftu, Bui, Balerobe, Mieso, Kulubi, Gashena, and Chaffedonsa, and -0.4, -4.0, and -3.4 degrees Celsius in Debrebrehan, Chelenko, and Haromaya, respectively. Conversely, there was cloud cover in some parts of the southwestern part of the country, and rain was recorded in Aman.

Weather Forecast for next day

Jan. 6, 2026

በነገው ዕለት በሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ መካከለኛው እና ምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ይኖራቸዋል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ በምስራቅ አማራ፣ መካከለኛው፣ ደቡብ ከፍተኛ ቦታዎች እና ምስራቅ ኦሮሚያ ላይ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች ሆኖ እንደሚመዘገብ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ በደቡብ ምዕራብ እና ደቡብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን የሚኖራቸው ሲሆን በጥቂት የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ሸካ እና ከፋ ዞኖች ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡

Tomorrow, the north west, northeast, central, and east parts of our country will experience dry, sunny, and windy Bega weather. Associated with this, numerical forecast information indicates that the minimum temperature of the day will be recorded below 5 degrees Celsius in east Amhara, central, south highlands, and east Oromia. On the other hand, there will be cloud coverage in the south west and south parts of the country; accordingly, a few areas of Jimma, Ilubabor, and Sheka and Kefa zones will have light rain.