Daily Weather Report 26 January 04
Weather Summary for previous day
በትናንትናዉ ዕለት በደቡብ፣ በደቡብምዕራብና በምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸዉ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ቴፒ እና ሀዋሳ ቀላል መጠን ያለው አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን፣በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው እና በምስራቅ የሀገርቱ አካባቢዎች ላይ የበጋዉ ደረቅ፣ ፀሐያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ የተስተዋለ ሲሆን፤ በወገልጤና፣ በደብረብርሀን፣ በጨለንቆ፣ በቁልቢ፣ በመሀልሜዳ፣ በደባርቅ፣ በአለም ከተማ፣ በቡኢ እና በዳንግላ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ 5 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday there were cloudy conditions with mist over the southern, southwestern, and western parts of the country. Along with this, light rain was reported in Tepi and Hawassa. On the other hand, the northern, northeastern, central, and eastern regions experienced a dry, sunny, and windy weather pattern. In Wegeltena, Debre Berhan, Chelenko, Kulubi, Mehal Meda, Debark, Alem Ketema, Bu'i, and Dangila, daytime minimum temperatures were recorded below 5 degrees Celsius.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብና ደቡብ ምስራቅ እንዲሁም በምዕራብ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጎፋ እና ባስኬቶ ዞኖች በጥቂት ቦታዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም የጅማ ዞን፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ከፋ ዞኖች በጥቂት ቦታዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡በሌላ በኩል በሰሜን፣በሰሜን ምስራቅ፣ በምስራቅ፣ በደቡብ ደጋማ ስፍራዎች፣ በምስራቅ እና በመካከለኛው የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ የሚስተዋል ሲሆን፤ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች ሆኖ የሚመዘገብ ሲሆንና፤ የሌሊትና የማለዳው ቅዝቃዜም እንደሚኖረው የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
Tomorrow, during the day, cloudy conditions are expected over the southern and south-eastern as well as the western and south-western parts of the country, which are the second rain-bearing areas in summer. In addition, light rain is expected in some locations of the Gofa and Basketo zones of the South Ethiopia Region. Likewise, in parts of the Jimma zone; Bench Sheko, West Omo, and Kaffa zones of South West Ethiopia; light, unseasonal rain is expected in some places. On the other hand, in the northern, north-eastern, eastern, south-central, eastern, and central parts of the country, dry, sunny and windy summer conditions will prevail. Daytime low temperatures are forecast to fall below 5 degrees Celsius, and predicted frost is expected during the night and early morning.