Daily Weather Report 26 January 03

Weather Summary for previous day

Jan. 2, 2026

በትናንትናዉ ዕለት በደቡብ፣ በደቡብምዕራብና በምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸዉ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ በቲንሹ ሜጥ እና በዲላ ቀላል መጠን ያለው አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን፣በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው እና በምስራቅ የሀገርቱ አካባቢዎች ላይ የበጋዉ ደረቅ፣ ፀሐያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ የተስተዋለ ሲሆን፤ በወገልጤና፣ በደብረብርሀን፣ በጨለንቆ፣ በቁልቢ፣ በመሀልሜዳ፣ ደብረ ማርቆስ፣ በአለም ከተማ፣ በቡኢ እና በዳንግላ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ 5 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday there were cloudy conditions over the southern, south-western and western parts of our country. In addition, light showers were reported in Tinshu Met and Dilla. On the other hand, the northern, north-eastern, central and eastern parts of the country experienced the typical dry, sunny and windy weather of the season; in Wegeltena, Debre Berhan,Chelenko,Kulubi,Mehal Meda,Debre Markos,Alem Ketema,Bui and Dangila the daytime low temperature was recorded below 5 degrees Celsius.

Weather Forecast for next day

Jan. 4, 2026

በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብና ደቡብ ምስራቅ እንዲሁም በምዕራብ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ኮንሶ እና ጌዲኦ ዞኖች እና የቦረና ዞን በጥቂት ቦታዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም የጅማ፤ ምስራቅ ትግራይ ፤ ምስራቅ ጎጃም ዞኖች፤ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ከፋ ዞኖች በጥቂት ቦታዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ፣ በምስራቅ፣ በደቡብ ደጋማ ስፍራዎች እና በመካከለኛው የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ የሚስተዋል ሲሆን፤ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች ሆኖ የሚመዘገብ ሲሆንና፤ የሌሊትና የማለዳው ቅዝቃዜም እንደሚኖረው የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡

Tomorrow during the daytime there will be cloudy conditions over southern and southeastern areas as well as over western and southwestern parts of the country. In addition, light rain is expected in a few places of South Ethiopia regions: Gamo,Gofa,Basketo,South Omo,Konso and Gedeo zones, and in some spots of the Borena zone. Light, sporadic rain is also expected in a few areas of the following zones: Jima, Eastern Tigray, East Gojjam, Bench Sheko, Konta, West Omo and Kefa. On the other hand, in the northern and eastern parts, in the eastern highlands, in the southern lowlands and in the central areas of the country, the weather will be dry, sunny and windy. The daytime minimum temperature is forecast to be below 5 degrees Celsius, and morning and nighttime frost is also expected according to the forecast information.