Daily Weather Report 26 January 02

Weather Summary for previous day

Jan. 1, 2026

በትናንትናዉ ዕለት በምዕራብ ኦሮሚያ፣ በጋምቤላ፣ በሲዳማ እና በደቡብ ኢትዮጵያ የደመና ሽፋን ነበራቸዉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በኢጃጅ፣ ሶኮሩ፣ ጌጫ፣ ሳውላ፣ ኮንሶ፣ ዲመካ፣ ብላቴ፣ ሀዋሳ እና ወንዶገነት ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በቡልቂ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ፣ በሰሜን ምዕራብ እና በምስራቅ የሀገርቱ አካባቢዎች ላይ የበጋዉ ደረቅ፣ ፀሐያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ የተስተዋለ ሲሆን፤ በአዲግራት፣ ኮረም፣ ደባርቅ፣ ዳንግላ፣ ወገልጤና፣ አለምከተማ፣ ደብረብርሀን፣ ጉዶበረት፣ ጨለንቆ እና ሐሮማያ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ 5 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች ሆኖ ተመዝግቧል ፡፡

Yesterday, there was cloud cover in the western Oromia, Gambella, Sidama, and southern Ethiopia. In this regards, light to moderate rainfall (1-29 mm) were received in Ejaji, Sokoru, Gecha, Sawla, Konso, Dimeka, Bilatte, Hawassa, and Wondogenet. Additionally, in Bulki recorded heavy rainfall exceeding 30 mm within 24 hours. On the other hand, the northeast, northwest, and eastern parts of the country experienced dry, sunny, and windy Bega weather condition, while the daily minimum temperature was recorded below 5 degree Celsius in In Adigrat, Korem, Debark, Dangla, Wegeltena, Alemketama, Debrebrihan, Gundoberet, Chelenko, and Haromaya.

Weather Forecast for next day

Jan. 3, 2026

በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብ የሀገሪቱ ክፍሎች እንዲሁም በደቡብ ምዕራብ፣ በምዕራብ እና በሰሜን ምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከኦሮሚያ ክልል የቦረና፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች በጥቂት ቦታዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም የጅማ እና ምዕራብ አርሲ ዞኖች፤ የሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ የምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜን እና ደቡብ ወሎ ዞኖች፤ የደቡብ ምስራቅ እና ደቡብ ትግራይ ዞኖች እና የቅልበቲ፣ ፋንቲ እና አውሲ ዞኖች በጥቂት ቦታዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜንምዕራብ፣ በመካከለኛው፣ በደቡብ ከፍተኛ ቦታዎች እና በምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የበጋ ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ የሚስተዋል ሲሆን በአንዳንድ ደጋማ ስፍራዎች ላይ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ 5 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች ሆኖ እንደሚመዘገብ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡

Tomorrow, there will be cloud cover in the southern parts of the country, which are the second rainy season of Bega, as well as in the southwest, west, and northeastern parts of the country. In association with this, from southern Ethiopia region Wolaita, Gofa, Basketo, and Gedeo zones; Sidama region zones; from Oromia region Borena, Guji and West Guji zones, will receive light amount of rainfall. Additionally, in Jimma and west Arsi zones; Sheka, Bench Sheko, Kefa, Konta, West Omo, and Dawro zones; east Gojjam, North and South Wollo zones; southeast and south Tigray Zone and Kilbeti, Fanti and Awsi zones will be light unseasonal rain in a few places. On the other hand, in the northwest, central, southern highlands, and eastern parts of the country will experience dry, sunny, and windy Bega weather, and in some highland areas, the daily minimum temperatures are expected to drop below 5 degree Celsius.