Daily Weather Report 26 January 01

Weather Summary for previous day

Dec. 31, 2025

በትናንትናዉ ዕለት በደቡብ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ የሀገርቱ ክፍሎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸዉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በጊዳ አያና፣ ጭራ፣ ማሻ፣ አማን፣ ማጂ፣ ጂንካ፣ ተርጫ፣ ኮንሶ፣ ዲላ፣ ምዕራብ አባያ፣ ቢላቴ፣ ገለምሶ፣ ድሬ ዳዋ፣ ሐረር፣ ጉበቲ፣ ይርጋለም፣ ሀሮረሳ፣ ዲመካ፣ መንድዳ፣ ኮሬም፣ ኩርፋ ጫሌ እና ሽንድ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ፣ በሰሜን እና በምስራቅ የሀገርቱ አካባቢዎች ላይ የበጋዉ ደረቅ፣ ፀሐያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ የተስተዋለ ሲሆን፤ ደባርቅ፣ ባህር ዳር፣ ዳንግላ፣ አምደ ወርቅ፣ ጨለንቆ፣ መሀል መዳ፣ ጉንዶ ቤሬት ፣ዳባቲ እና ኮሶበር የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ 5 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች ሆኖ ተመዝግቧል ፡፡

Yesterday, there was cloud coverage over the southern, southwestern and eastern parts of the country. In this regard, light to moderate (1-29 mm) rainfall was recorded in Gida Ayana, Cira, Masha, Aman, Maji, Jinka, Tercha, Konso, Dilla, Mirab Abay, Bilate, Gelemso, Dire Dawa, Harar, Gubeti, Yirgalem, Haroresa, Dimeka, Mendida, Korem, Kurfa Chale and Shind. On the other hand, dry, sunny and windy summer weather was observed in the north eastern, northern and eastern parts of the country; Debark, Bahir Dar, Dangila, Amde Work, Chelenko, Mehal Meda, Gundo Beret, Dabati and Kosober, the daily minimum temperature was recorded below 5 degrees Celsius.

Weather Forecast for next day

Jan. 2, 2026

በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብ የሀገሪቱ ክፍሎች እንዲሁም በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም አልፎ አልፎ ከሚኖረው የደመና ሽፋን በመነሳት የጅማ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ሰሜን ሸዋ፣ ባሌ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ ዞኖች፤ የሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ቀቤና ልዩ ዞን፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀላባ፣ ከምባታ እና ጠንባሮ ዞኖች፤ የሰሜን ወሎ፣ ደቡብ ወሎ፣ ደቡብ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች፤ ከ የምስራቅ ትግራይ ዞን እና የቅልበቲ ዞን ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን እና በምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የበጋ ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ የሚስተዋል ሲሆን የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ 5 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች ሆኖ እንደሚመዘገብ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

For tomorrow, the southern parts of the country, which are in their second rainy season of the summer, as well as the north eastern, central and southwestern parts of the country, will have cloud cover. In line with this, light rain will be experienced in the Guji and West Guji zones of the Oromia region; Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, South Omo and Gedio zones of the Southern Ethiopia region; and Sidama region. In addition, due to the occasional cloud coverage, the Jimma, West, South West and North Shewa, Bale, Arsi and West Arsi zones; Sheka, Bench Sheko, Kefa, Konta, West Omo and Dawro zones; Gurage, East Gurage, Silte, Hadiya, Kebena Special Zone, Yem Special Zone, Halaba, Kembata and Tanbaro zones; North Wollo, South Wollo, South Gondar, West and East Gojam zones; East Tigray zone and Kelbeti zone will experience light to moderate (1-29 mm) unseasonal rainfall. On the other hand, as forecast data indicate Bega’s dry, sunny and windy weather will be observed in the north eastern and eastern parts of the country, with the minimum temperature of the day being recorded below 5 degrees Celsius.