Daily Weather Report 26 February 27

Weather Summary for previous day

Feb. 26, 2026

በትናንትናው ዕለት በሰሜን ምዕራብ፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው፣ በደቡብ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በጎንደር፣ ነፋስ መውጫ፣ ጋሳይ፣ ላሊበላ፣ ሻምቡ፣ ሳውላ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ብላቴ፣ ኮንሶ እና ዳራማሎ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው እናብ የተመዘገበ ሲሆን በቡልቂ እና ጅማ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል መተማ፣ አዲስ ዘመን፣ ሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ገዋኔ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35-39.6 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ተመዝቧል፡፡

Yesterday, cloud cover was observed over the northwestern, northeastern, central, southern, and southwestern parts of Ethiopia. Accordingly, light to moderate rainfall was recorded in Gondar, Nefase Mewcha, Gasay, Lalibela, Shambu, Sawla, Wolaita Sodo, Bilatte, Konso, and Daramalo. In addition, heavy rainfall exceeding 30 mm was recorded in Bulki and Jimma. On the other hand, the daily maximum temperatures ranging from 35°C to 39.6°C were recorded at Metema, Addis Zemen, Semara, Elidar, Gewane, Gode, and Kebridehar.

Weather Forecast for next day

Feb. 28, 2026

በነገው ዕለት በልግ ዋነኛ እና ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የተስፋፋ የደመና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ በመሆኑም ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ጌድኦ፣ አሌ፣ ኮሬ፣ ጋርዱላ፣ ቡርጂ፣ ደቡብ ኦሞ እና ኮንሶ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ባሌ፣ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የየም ልዩ ዞን፣ ስልጤ፣ ሀድያ እና ከምባታ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የዳውሮ ዞን እና ከአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ዞን፣ ከትግራይ ክልል የማዕከላዊና ምስራቅ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በጥቂት የጉጂና የቦረና ዞኖች ላይ በ24 ሠዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ አሶሳ፣ ሸርኮሌ፣ ኩምሩክ፣መተማ፣ አዋሽ አርባ፣ ገዋኔ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ34-40 ዲግሪ ሴልሽየስ እንደሚሆን አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡

Tomorrow, there will be widespread cloud cover over the Belg main and second rainy seasons of our country. Therefore, from the Southern Ethiopia Region, Wolaita, Gamo, Gofa, Gedeo, Ale, Kore, Gardula, Burji, South Omo and Konso zones; from the Oromia Region, West and East Hararge, Arsi and West Arsi, Bale, Guji and West Guji, Borena and East Borena zones; Sidama Region zones; The Yem Special Zone, Silte, Hadiya and Kembata zones of the Central Ethiopian Region; the Dawro Zone of the Southwestern Ethiopian Region and the South Gondar Zone of the Amhara Region; and the Central and Eastern Zones of the Tigray Region will receive light to moderate (1-29 mm) rainfall. In addition, a few Guji and Borena zones will receive heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours. On the other hand, numerical forecast indicates that the maximum temperature of the day in Gambella, Fundo, Abobo, Asosa, Sherkole, Kurmuk, Metema, Awash Arba, Gewane, Gode and Kebridehar will be between 34-40 degrees Celsius.