Daily Weather Report 26 February 24

Weather Summary for previous day

Feb. 23, 2026

በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ በደቡብ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በአርባምንጭ፣ ኮንሶ፣ ዲመቃ እና ጊዶሌ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን በቡልቂ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ መንደር11፣ ማይሃንሳ፣ የጭላ፣ አዲስ ዘመን፣ መተከል፣ ሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ገዋኔ፣ አዋሽ አርባ፣ መተሐራ፣ ቀብሪደሃር እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35-43.5°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, there was cloud cover over the western, southern and southwestern parts of the country. Along with this, light rain was recorded in Arbaminch, Konso, Dimeka and Gidole, while heavy rain was recorded in Bulki. On the other hand, in Gambella, Fugendo, Village11, Mayhansa, Yechila, Addis Zemen, Metekel, Semera, Elidar, Gewane, Awash Arba, Metahara, Kebridehar and Gode, the maximum temperature of the day was recorded at 35-43.5°C.

Weather Forecast for next day

Feb. 25, 2026

በነገው ዕለት በደቡብ፣ በደቡብ ምዕራብ፣ በምዕራብ፣ በመካከለኛው፣ በሰሜን ምዕራብ እና በሰሜን ምስራቅ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ በመሆኑም ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጌድኦ፣ አሌ፣ ኮሬ፣ ጋርዶላ፣ ቡርጂ እና ኮንሶ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ባሌ፣ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና ዞኖች፤ በሁሉም ሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የዳውሮ ዞን፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀድያ፣ ሀላባ፣ ስልጤ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፣ ከአማራ ክልል ሰሜንና ደቡብ ጎንደር ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የዳዋ፣ ሊበን እና አፍዴር ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ ላሬ፣ አቦቦ፣ መተማ፣ ማንኩሽ፣ አሶሳ፣ ኩምሩክ፣ ሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ገዋኔ፣ አዋሽ አርባ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35-39 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ እንደሚመዘገብ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

Tomorrow, there will be cloud cover in the south, southwest, west, central, northwest and northeast parts of our country. Therefore, in the Southern Ethiopia Region, Wolaita, Gamo, Gedeo, Ale, Kore, Gardola, Burji and Konso zones; in the Oromia Region, Jimma, West Arsi, Bale, Guji and West Guji, Borena and East Borena zones; All zones of Sidama Region; Dawro Zone of Southwestern Ethiopia Region; Hadiya, Halaba, Silte, Kembata and Tembaro Zones of Central Ethiopia Region; North and South Gondar Zones of Amhara Region; and Dawa, Liben and Afder Zones of Somali Region will experience light to moderate (1-29mm) rainfall. On the other hand, Gambella, Fugendo, Lare, Abobo, Metema, Mankush, Asosa, Kumruk, Semera, Elidar, Gewane, Awash Arba, Gode and Kebridehar will experience high temperatures of 35-39 degrees Celsius, forecast indicates.