Daily Weather Report 26 February 23
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በደቡብ ምዕራብ፣ በደቡብ እና በሰሜን ምስራቅ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ በቴፒ፣ ወላይታሶዶ፣ ሳውላ፣ አርባምንጭ፣ ጂንካ፣ ጊዶሌ፣ ዳራማሎ፣ ዲመካ፣ ቡልቂ፣ ቡሌሆራ፣ ጨፋ እና ትንሹሚጢ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በመተማ፣ አሸሬ፣ አዲስ ዘመን፣ ፓዌ፣ ማይሀንሳ፣ የጭላ፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ ሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ገዋኔ፣ አዋሽ አርባ፣ ቀብሪደሀር እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.0-41.5 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, there was cloud cover across the southwest, south, and northeast parts of the country. As a result, light to moderate rainfall (1-29 mm) was recorded in Tepi, Wolaitasodo, Sawla, Arbaminch, Jinka, Gidole, Daramala, Dimeka, Bulki, Bulehora, Cheffa, and Tinshu Miti. On the other hand in Metema, Ashere, Addis Zeman, Pawe, Mayhansa, Yechila, Gambella, Fugnido, Semara, Elidar, Gewane, Awash Arba, Kebridehar, and Gode, the daily maximum temperature ranged from 35.0 to 41.5 degrees Celsius.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በደቡብ፣ በደቡብ ምዕራብ፣ በምዕራብ፣ በመካከለኛው እና በሰሜን ምስራቅ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የተሻለ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ በመሆኑም ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ፣ ጌዴኦ፣ ደቡብ ኦሞ፣ አሌ፣ ኮሬ፣ ጋርዶላ፣ ቡርጅ እና ኮንሶ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ባሌ፣ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና ዞኖች፤ በሁሉም ሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ቤንች ሸኮ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ኮንታ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀድያ፣ ሀላባ፣ ስልጤ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የዳዋ ዞን ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በዲሎ፣ ዲሬ፣ ሚዮ፣ ሞያሌ እና ጉች በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በሌላ በኩል በ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ ላሬ፣ አቦቦ፣ መተማ፣ ማንኩሽ፣ ሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ገዋኔ፣ አዋሽ አርባ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35-39 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ እንደሚመዘገብ የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
Tomorrow, there will be better cloud cover over the southern, southwestern, western, central, and northeastern areas of our country. Accordingly, from the southern Ethiopian region Gofa, Gamo, Basketo, Gedio, South Omo, Alle, Kore, Gardula, Burj, and Konso zones; from Oromia region, Jimma, Arsi, West Arsi, Bale, Guji, West Guji, Borena, and East Borena zones; from Southwest region of Ethiopia, Bench Sheko, West Omo, Konta, and Dawro zones; from Central Ethiopian region Hadiya, Halaba, Silte, Kembata, and Tembaro zones; and from Somali region Dawa zone, will receive light to moderate rainfall (1-29 mm). Additionally, in Dillo, Dire, Moyale, and Guich will experience heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours. On the other hand, in Gambella, Fugnido, Lare, Abobo, Metema, Mankush, Semara, Elidar, Gewane, Awash Arba, Gode, and Kebridehar the daily maximum temperature will be recorded at 35-39 degrees Celsius.