Daily Weather Report 26 February 22
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በምዕራብ ኦሮሚያ፣ በጋምቤላ፣ በደቡብ ምዕራብ እና በደቡብ ኢትዮጵያ አካባቢዎች ላይ የተሻለ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ በመሆኑም በጅማ፣ ሶኮሩ፣ ቅዳሜ ገበያ፣ ኩሚ፣ ትንሹሚጢ፣ ቴፒ፣ ተርጫ፣ ሳውላ፣ ጂንካ፣ አርባምንጭ እና ቡርጅ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በመተማ፣ ጋምቤላ እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን 35.0 ዲግሪ ሴልሽየስ በላይ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, better cloud cover was observed across the western Oromia, Gambella, southwestern, and southern Ethiopia. Accordingly, light to moderate rainfall (1–29 mm) was recorded in Jimma, Sokoru, Kidame Gebeya, Kumi, Tinshu Miti, Tepi, Tercha, Sawla, Jinka, Arba Minch, and Burji. On the other hand, in Metema, Gambella, and Gode, the daily maximum temperature exceeded 35.0°C.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በደቡብ ምዕራብ፣ በደቡብ፣ በመካከለኛው እና በምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ፣ ጌዴኦ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ቡርጅ እና ኮንሶ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ባሌ፣ ቦረና፣ ጉጂ እና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ቤንች ሸኮ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ኮንታ እና ዳውሮ ዞኖች እና ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀድያ፣ ሀላባ፣ ጉራጌ፣ ስልጤ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በመተማ፣ ማንኩሽ፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ ላሬ፣ አቦቦ፣ ሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ገዋኔ፣ አዋሽ አርባ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35-39 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ እንደሚመዘገብ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡
Tomorrow, cloud cover is expected over the southwestern, southern, central, and western parts of the country. Accordingly, from South Ethiopia region Wolaita, Gofa, Gamo, Basketo, Gedeo, South Omo, Burji, and Konso Zones; from Oromia Region Jimma, Ilubabor, Arsi, West Arsi, Bale, Borena, Guji, and West Guji Zones; from Southwest Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, West Omo, Konta, and Dawro Zones; from Central Ethiopia region Hadiya, Halaba, Gurage, Silte, Kembata, and Tembaro Zones will receive light to moderate rainfall (1-29 mm) rainfall. On the other hand, in Metema, Mankush, Gambella, Fugnido, Lare, Abobo, Semera, Elidar, Gewane, Awash Arba, Gode, and Kebridehar, the daily maximum temperature is expected to range between 35°C and 39°C.