Daily Weather Report 26 February 21
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በደቡብ ምዕራብ፣ በምዕራብ እና በደቡብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ በጎሬ፣ በደሌ፣ ጅማ፣ ቡሌሆራ፣ አማን፣ ሳውላ፣ አርባምንጭ፣ ቡርጅ እና ደብረማርቆስ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በምዕራብ አባያ እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን 35.0 ዲግሪ ሴልሽየስ በላይ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, cloud cover was observed across the southwest, west, and southern parts of the country. In association with this, light to moderate (1-29 mm) rainfall was recorded in Gore, Bedele, Jimma, Bule Hora, Aman, Sawla, Arbaminch, Burji, and Debre Markos. On the other hand, in Mirab Abaya and Gode the daily maximum temperature was recorded above 35.0 degrees Celsius.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በደቡብ፣ በደቡብ ምዕራብ፣ ምዕራብ እና በመካከለኛው የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ በመሆኑም ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ቦረና፣ ጉጂ እና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጎፋ፣ ጋሞ፣ ወላይታ፣ ጌዴኦ፣ ደቡብ ኦሞ እና ባስኬቶ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ቤንች ሸኮ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ኮንታ እና ዳውሮ ዞኖች እና ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀድያ፣ ሀላባ፣ ስልጤ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ ላሬ፣ አቦቦ፣ መተማ፣ ማንኩሽ፣ ሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ገዋኔ፣ አዋሽ አርባ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35-39 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ እንደሚመዘገብ የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
Tomorrow, cloud cover is expected over the southern, southwestern, western, and central parts of the country. Accordingly, Light to moderate (1-29 mm) amount of rainfall is expected in Jimma, West Arsi, Borena, Guji, and West Guji zones of Oromia region; in Gofa, Gamo, Wolaita, Gedeo, South Omo, and Basketo zones of South Ethiopia region; in all zones of the Sidama region; in Bench Sheko, West Omo, Konta, and Dawro zones of Southwest Ethiopia region; and of Hadiya, Halaba, Silte, Kembata, and Tembaro zones of the central Ethiopian regions. On the other hand, the forecast indicates that in Gambella, Fugnido, Abobo, Lare, Metema, Mankush, Semera, Elidar, Gewane, Awash Arba, Gode, and Kebridehar the daily maximum temperature will be 35-39°C.