Daily Weather Report 26 February 20

Weather Summary for previous day

Feb. 19, 2026

በትናንትናዉ ዕለት በደቡብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምዕራብ እና መካከለኛዉ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸዉ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ በጋቲራ፣ ጭራ፣ ጅማ፣ ቦሬ፣ ቡሊቅ እና ዳራማሎ ቀላል መጠን ያለዉ ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በላሬ፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ ኤሊዳር፣ ገዋኔ፣ አዋሽ አርባ፣ አዲስ ዘመን፣ የጪላ፣ አሸሬ፣ ቢላቴ፣ ቡርጂ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.1-41.8 ዲግሪ ሴልሺየስ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, there was cloud cover over the southern, southwestern, western and central regions of our country. Along with this, light rain was recorded in Gatira, Fugnido, Jimma, Bore, Bulki and Daramalo. On the other hand, in Lare, Gambella, Fugnido, Elidar, Gewane, Awash Arba, Addis Zemen, Yechila, Ashre, Bilate, Burji, Gode and Kebridehar, the maximum temperature of the day was recorded as 35.1-41.8 degrees Celsius.

Weather Forecast for next day

Feb. 21, 2026

በነገው ዕለት በደቡብ፣ በደቡብ ምዕራብ እና በመካከለኛዉ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የተሻሌ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ አለ፣ ጋርዶላ፣ ጌዴኦ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ኮሬ እና ባስከቶ ዞኖች፤ ሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፣ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ምዕራብ ጉጂ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂ፣ ባሌ እና ቦረና ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ኮንታ፣ እና ዳዉሮ ዞኖች እና ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የስልጤ፣ የም ልዩ ዞን እና ሀላባ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለዉ ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ ላሬ፣ አቦቦ፣ መተማ፣ ማንኩሽ፣ ኩሙሩክ፣ ሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ገዋኔ፣ አዋሽ አርባ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ እንደሚመዘገብ ሀሂዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

Tomorrow, there will be better cloud cover over the southern, southwestern and central parts of our country. In this regard, the Wolaita, Gamo, Gofa, Ale, Gardolla, Gedeo, South Omo, Kore and Basketo zones of the Southern Ethiopian Region; all zones of Sidama Region; the Jimma, West Guji, West Arsi, Guji, Bale and Borena zones of the Oromia Region; the Kefa, Bench Sheko, Sheka, West Omo, Konta and Dawro zones of the Southwestern Ethiopian Region; and the Silte, Yem special Zone and Halaba zones of the Central Ethiopian Region will experience light to moderate rain. On the other hand, weather forecast data shows that the maximum daily temperature will be recorded above 35 degrees Celsius in Gambella, Fundo, Lare, Abobo, Metema, Mankush, Kurmuk, Semera, Elidar, Gewane, Awash Arba, Gode and Kebridehar.