Daily Weather Report 26 February 19

Weather Summary for previous day

Feb. 18, 2026

በትናንትናው ዕለት በደቡብ ምዕራብ፣ በምዕራብ እና በደቡብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ በሊሙገነት፣ ነቀምቴ፣ አማን፣ ቴፒ እና ሽንዲ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በመተማ፣ ፓዌ፣ መሆኒ፣ ማይሀንሳ፣ የጭላ፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ ጨዋቃ፣ ብላቴ፣ ምዕራብ አባያ፣ ሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ገዋኔ፣ አዋሽ አርባ፣ ቀብሪደሀር እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን 35.0-42.5 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, cloud cover was observed across the southwest, west, and southern parts of the country. In association with this, light rainfall was recorded in Limu Genet, Nekemte, Aman, Tepi, and Shindi. On the other hand, in Metema, Pawe, Mehoni, Mayhansa, Yechila, Gambella, Fugnido, Chewaka, Bilatte, Mirab Abaya, Semera, Elidar, Gewane, Awash Arba, Kebridehar, and Gode, daily maximum temperatures ranged between 35.0°C and 42.5°C.

Weather Forecast for next day

Feb. 20, 2026

በነገው ዕለት በደቡብ፣ በደቡብ ምዕራብ፣ ምዕራብ እና በመካከለኛው የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጎፋ፣ ጋሞ፣ ወላይታ፣ ጌዴኦ፣ ደቡብ ኦሞ እና ባስኬቶ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ምዕራብ አርሲ እና ጉጂ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ኮንታ እና ዳውሮ ዞኖች እና ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ እና ማጃንግ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በመተማ፣ማንኩሽ፣ ኩምሩከ፣ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ ላሬ፣ አቦቦ፣ ሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ገዋኔ፣ አዋሽ አርባ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 ዲግሪ ሴልሽየስ በላይ እንደሚመዘገብ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

Tomorrow, cloud cover is expected over the southern, southwestern, western, and central parts of the country. Accordingly, light to moderate rainfall is expected in the Gofa, Gamo, Wolaita, Gedeo, South Omo, and Basketo zones of the Southern Ethiopia region; zones of the Sidama region; in Jimma, Ilubabor, West Arsi, and Guji zones of the Oromia region; in Kefa, Bench Sheko, Sheka, West Omo, Konta, and Dawro zones of Southwest Ethiopia region, as well as in Agnuak and Majang zones of the Gambella region. On the other hand, the forecast indicates that in Metema, Mankush, Kurmuk, Gambella, Fugnido, Abobo, Lare, Semera, Elidar, Gewane, Awash Arba, Gode, and Kebridehar, the daily maximum temperature exceed 35°C.