Daily Weather Report 26 February 18
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በደቡብ፣ በደቡብ ምዕራብ እና በምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ በመሆኑም በሊሙገነት፣ ቡሌሆራ፣ አሽ፣ አማን፣ ማጂ፣ ሳውላ፣ ጂንካ፣ ዲመካ እና ጊዶሌ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በመተማ፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ ጨዋቃ፣ ብላቴ፣ ምዕራብ አባያ፣ ሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ገዋኔ፣ አዋሽ አርባ፣ ቀብሪደሀር እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን 35.0-42.0 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, cloud cover was observed acro the southern, southwestern and western parts of the country. In this regard, light to moderate amount of rainfall was recorded in Limugent, Bulehore, Ashi, Aman, Maji, Sawla, Jinka, Dimeka and Gidole. On the other hand, in Metema, Gambella, Fugnido, Chewaka, Bilate, Mirab Abaya, Semera, Elidar, Gewane, Awash Ariba, Kebridehar and Gode, the daily maximum temperature ranged from 35 to 42.0°C.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በምዕራብ፣ በደቡብ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ እና ኢሉባቦር ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጎፋ፣ ጌዴኦ፣ ደቡብ ኦሞ እና ባስኬቶ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ ላሬ፣ አቦቦ፣ ማንኩሽ፣ ኩምሩከ፣ መተማ፣ ማይሀንሳ፣ ሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ገዋኔ፣ አዋሽ አርባ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 ዲግሪ ሴልሽየስ በላይ እንደሚመዘገብ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
Tomorrow, cloud cover is expected over the southern, southwestern, and western parts of the country. In this regard, light to moderate amounts of rainfall are expected in Jimma and Ilubabor zones of the Oromia region; Gofa, Gedeo, South Omo, and Basketo zones of the South Ethiopia region; the Sidama region zones; and Bench Sheko, Sheka, West Omo, and Dawro zones of the Southwest Ethiopia region. On the other hand, numerical forecast data indicate that the daily maximum temperature will exceed 35°C in Gambella, Fugnido, Lare, Abobo, Mankush, Kurmuk, Metema, Mayhansa, Semera, Elidar, Gewane, Awash Arba, Gode, and Kebridehar.