Daily Weather Report 26 February 17
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በደቡብ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ በጋቲራ፣ ጭራ እና ማሻ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ ማይሀንሳ፣ መተማ፣ አዲስ ዘመን፣ ሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ገዋኔ፣ አዋሽ አርባ፣ ድሬዳዋ እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን 35.0-40.5 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, cloud cover was observed acro the southern and southwestern parts of the country. In this regard, light to moderate rainfall was recorded in Masha, Chira, and Gatira. On the other hand, in Gambella, Fugnido, Mayhansa, Metema, Addis Zemen, Semera, Elidar, Gewane, Awash Ariba, Dire Dawa and Gode, the daily maximum temperature ranged from 35 to 40.5°C.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በደቡብ ምዕራብ፣ በደቡብ እና በምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጌዴኦ፣ ደቡብ ኦሞ እና ባስኬቶ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ ዞን፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ከፋ፣ ቤንች ሸኮ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ ላሬ፣ አቦቦ፣ መተማ፣ ማይሀንሳ፣ ሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ገዋኔ፣ አዋሽ አርባ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 ዲግሪ ሴልሽየስ በላይ እንደሚመዘገብ የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
Tomorrow, cloud cover is expected over the southern, southwestern, and western parts of the country. In this regard, light to moderate rainfall is anticipated in Gedeo, South Omo, and Basketo zones of the Southern Ethiopia region; Jimma zone of the Oromia region; zones of the Sidama region, and Sheka, Kefa, Bench Sheko, West Omo, and Dawuro zones of southwestern. On the other hand, the numerical forecast indicates that the daily maximum temperature will exceed 35°C in Gambella, Fugnido, Lare, Abobo, Metema, Mayhansa, Semera, Elidar, Gewane, Awash Arba, Kebridehar, and Gode.