Daily Weather Report 26 February 16

Weather Summary for previous day

Feb. 15, 2026

በትናንትናው ዕለት በደቡብ፣ በደቡብ ምዕራብ እና በምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ በማጂ፣ ጭራ እና በጋቲራ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ ላሬ፣ አቦቦ፣ ማይሀንሳ፣ ጨዋቃ፣ ብላቴ፣ የጭላ፣ መተማ፣ ሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ገዋኔ፣ አዋሽ አር፣ ጎዴ እና በቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን 35.0-40.0 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, cloud cover was observed over the southern, southwestern and western parts of the country. In this regard, light to moderate rainfall was recorded in Maji, Chira, and Gatira. On the other hand, in Gambella, Fugnido, Lare, Abobo, Mayhansa, Yechila, Chewaka, Bilate, Metema, Semera, Elidar, Gewane, Awash Ariba, Kebridehar and Gode, the daily maximum temperature ranged from 35 to 40.0°C.

Weather Forecast for next day

Feb. 17, 2026

በነገው ዕለት በደቡብ፣ በደቡብ ምዕራብ እና በምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የምዕራብ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጋሞ፣ ጎፋ፣ ጌዴኦ፣ ደቡብ ኦሞ እና ባስኬቶ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ቤንች ሸኮ፣ ሸካ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች በጥቂት ቦታዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ ላሬ፣ አቦቦ፣ መተማ፣ ሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ገዋኔ፣ አዋሽ አርባ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35°C በላይ እንደሚመዘገብ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

Tomorrow, cloud cover is expected over the southern, southwestern, and western parts of the country. Accordingly, light to moderate rainfall is anticipated in West Arsi, Guji and west Guji zones of the Oromia Region; Gamo, Gofa, Gedeo, South Omo, and Basketo zones of the South Ethiopia Region; Sidama region zones, and Bench Sheko, Sheka, Kefa, and West Omo zones of the Southwest Ethiopia Region. On the other hand, the numerical forecast indicates that the daily maximum temperature will exceed 35°C in Gambella, Fugnido, Lare, Abobo, Metema, Semera, Elidar, Gewane, Awash Arba, Kebridehar, and Gode.