Daily Weather Report 26 February 15

Weather Summary for previous day

Feb. 14, 2026

በትናንትናው ዕለት በደቡብ፣ በደቡብ ምዕራብ፣ በምዕራብ እና በመካከለኛው የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ በጂንካ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን 38.0°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday there were cloudy conditions over the southern, southwest, west, and central parts of our country. Along with this, moderate rainfall was recorded in and around Jinka. On the other hand, Gode recorded a daytime maximum temperature of 38.0°C.

Weather Forecast for next day

Feb. 16, 2026

በነገው ዕለት በደቡብ፣ በደቡብ ምዕራብ እና በምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ጉጂ እና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ፣ደቡብ ኦሞ እና ጌድኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀላባ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች ፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ ላሬ፣ አቦቦ፣ መንደር11፣ መተማ፣ ቀብሪደሃር፣ ጎዴ፣ ሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ገዋኔ እና አዋሽ አርባ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35°C በላይ እንደሚመዘገብ የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡

Tomorrow cloudy skies are expected over the southern, south‑western and western parts of the country. In connection with this, the western Arsi, Jimma, Guji and West Guji zones of Oromia; the Wolayta, Gofa, Gamo, Basketo, South Omo and Gedeo zones of Southern Ethiopia Region; the Sidama zones; the Halaba, Yem special zone, Hadiya, Kembata and Tambaro zones of Central Ethiopia Region; and the Bench Sheko, Sheka, Keffa, Konta, West Omo and Dawuro zones of South West Ethiopia are expected to receive light to moderate rainfall. On the other hand, Gambela, Fugnido, Lare, Abobo, Mender 11, Metema, Kebridahar, Gode, Semera, Elidar, Gewane and Awash Arba are forecast to record daytime high temperatures exceeding 35°C.